Translation is not possible.

አንዳንዴ ፈገግ ብንልስ ?

“በጥሩ የፍቅር ግንኙነት እንዴት መኖር ትችላላችሁ?” በሚል አንድ የሴቶች ዝግጂት ላይ በርከት ያሉ ባለ ትዳር ሴቶች ተገኝተው ነበር።

ሴቶቹም እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፦

“ምን ያህሎቻችሁ ባላችሁን ታፈቅራላችሁ?”

>>>ሁሉም እጃቸውን አወጡ

ተከታዩም ጥያቄ ፦ “ለመጨረሻ ጊዜ ለባሎቻችሁ

እንደምታፈቅሯቸው የገለፃችሁት መቼ ነው?”

>>> አንዳንዶቹ “ዛሬ”፣ የተወሰኑት “ትላንት” ፣ ቀሪዎቹ እንደማያስታውሱት ተናገሩ።

ከዛም ሴቶቹ በስልካቸው ሜሴጅ የሚከተለውን መልእክት ለባሎቻቸው እንዲልኩ ተጠየቁ፦

“የኔ ጣፋጭ ፣ በጣም አፈቅርሃለሁ"

ከባሎቻቸው ከተመለሱት መልሶች በከፊል፦

1- ደግሞ ዛሬ ምን ተፈጠረ? መኪናውን ዛሬም አጋጨሽው?

2- እህ ፣ የልጆቼ እናት፣ ዛሬ በጤናሽ ነው?

3- አልገባኝም ! ምንድነው ማለት የፈለግሽው?

.

4- አሁን ምን አያደረግሽ ነው? ዛሬ እንኳ በጭራሽ አንላቀቅም።

5- ደሞዝ ገና እኮ ነን አልደረሰም?

6- በይ አሁን ዙሪያ ጥምጥም አትሂጂ ፣ ዝም ብለሽ ምን ያህል እንደምትፈልጊ ብቻ ንገሪኝ!

7- ምንድነው? በህልሜ ነው?

8- ይሄን ሜሴጅ ለማን ልትልኪው እንደነበር ካልነገርሽኝ ዛሬ ገደልኩሽ!!!

9- በቀን እንዳትጠጪ ተነጋግረን አልነበር? እባክሽ አሁንም ከዚህ በላይ አትጠጪ!!

ምርጡ መልስ ፦..

10- ይቅርታ ፣ ማን ልበል?

ክክክ....

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄

https://t.me/FKR_ESKE_JENET

Send as a message
Share on my page
Share in the group