Çeviri imkansız.

" ለአረብ ሀገራት መሪዎች ጦርነቱን በርግጠኝነት በቴሌቪዥኖቻችሁ እየተመለከታችሁት ነው ። እኛ እናንተ መሳሪያችሁን ጦራችሁን አንቀሳቅሳችሁ በጋዛ ስለ ህፃናትና ስለ ኢስላም እንድትታገሉልን አንጠይቃችሁም ! ስለ የቅዱስ ቅዱስ ስለሆኑት ቅዱሳን ቦታዎቻችሁም እንድትታገሉልን አንጠይቃችሁም ! ሰለ ነብያችሁ ሶ.ዐ.ወ መሰደብም በቁጣ እንድትንቀሳቀሱ አንጠይቃችሁም ! ይህንን አንጠይቃችሁም ! እኛው ራሳችን ተሸክመነዋል ! በምንችለው ባለን አቅም እዚሁ በሰራናት መሳሪያችን ስለድናችን ስለቅዱሳን ቦታዎቻችን ስለ ውዱ ነብያችን ክብር እየተጋደልን ነው !

እንደው እኛ ያልገባንና የምንጠይቃችሁ ለሙስሊም ወንድሞቻችሁ የሰብአዊ እርዳታ መኪና መላክ አቃታችሁን ? ይህንን ማድረግ አቃታችሁን ?? "

ይህ የሀማሱ ቃል አቀባይ የአቡኡበይዳ ለአረብ መሪዎችና ህዝቦች የቀረበ ጥያቄ ነው !

በርግጥ እንደ አረቦች አሳፋሪ መሪም ሆነ አሳፋሪ ህዝብ በአሁኑ ሰአት የትም የለም !

2 görüntüleme
Mesaj olarak gönder
Sayfamda paylaş
Grupta paylaş