1 year Translate
Translation is not possible.

ንፍቅና ሩቅ አይደለም። ብዙዎቻችን ንፍቅና ሲባል ለሆነ የተመደበ ቡድን ብቻ የሚመለከት ይመስለናል። ነገርግን ለአንድ አማኝ ከንፍቅና በላይ የሚቀርበው የለም።

ዐሊ አቡጧሊብን (ረዐ) «ንፍቅና ምንድነው?» ብለው ጠየቋቸው። ዐሊም (ረዐ) ሲመልሱ «ንፍቅና ማለት ሰውየው በሚናገረውና በሚሰራው መካከል ልዩነት መኖሩ ነው» አሉ።

ይህ የዐሊ (ረዐ) ገለፃ በጣም ጥልቅ አረዳድ ሲሆን አብዛኞቻችን በምንናገረውና በምንሰራው መካከል ልዩነት በመኖሩ ንፍቅና ከእኛ በላይ ለማን ቅርብ ሰው እንደሌለው አስረጅ ነው።

ሰሃባዎች ይህ ጉዳይ ስለገባቸውም ነበር ጀነት የተመሰከረላቸው እንኳን ንፍቅናን ይጠረጥሩ የነበሩት። ታዲያ እኛስ ለምን ሩቅ አድርገን እናስበዋለን?

ንፍቅናን በነፍሱ ላይ መጠርጠር የአንድ አማኝ ባህሪ ነው። ሰሃባዎች እንኳን በሚፈሩት ጉዳይ ራሱን የሚያጥራራ ካለም እሱ የነገሩ ጥልቀት ያልተገነዘበ ነው። እናም አንድ ሰላት ባዘገያችሁ ጊዜ እንኳን ንፍቅናን ጠርጥሩት።

ሐሰን አል-በስሪ ሲናገሩ አሉ፦

«ንፍቅና አለብኝ ብሎ የሚጠረጥር የለም ሙዕሚን ቢሆን እንጅ። ንፍቅና የለብኝም ብሎ የማይጠረጥርም የለም ሙናፍቅ ቢሆን እንጅ።»

Send as a message
Share on my page
Share in the group