Translation is not possible.

አሁናዊ አጫጭር መረጃዎች:

▶️በቱርክ ፕሬዚደንት ውስጥ የደህንነት እና የውጭ ፖሊሲ ኮሚቴ አባል አል-ኑር ሻፊቅ እንደገለፁት የቱርክ ፕሬዝዳንት እስራኤልን በአለም አቀፍ ህግ ለመክሰስ ህጎችን እየገመገመ ነው ያሉ ሲሆን፣አሜሪካም ካለቅድመ ሁኔታ ለእስራኤል በሰጠችው የጦር ድጋፍ ጥፋተኛ ነች ብለዋል።

▶️ሃማስ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሰብአዊ ሚና ያላቸውን ሆስፒታሎች ለመጠበቅ ሁሉም ሀገራት እና አለም አቀፍ ተቋማት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን በማለት ጥሪ አስተላልፏል።

▶️የእስራኤል ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደዘገበው የእስራኤል የመንገደኞች አይሮፕላን እንዳያርፍ በመቃወም የዳግስታን ዜጎች ወደ ማካችካላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲገቡ የሚያሳዩ ምስሎችን አሳትሟል።

▶️የሩስያ ሚዲያ እንደዘገበው የእስራኤል የመንገደኞች አውሮፕላን በማካችካላ ካረፈ እና ተቃዋሚዎች ከወረሩት በኋላ የዳግስታን ባለስልጣናት የዋና ከተማይቱን ማካችካላ አየር ማረፊያ ለመዝጋት መገደዳቸውን ዘግቧል።

(NB:ዳግስታን“የተራሮች ምድር”የሚል ትርጓሜ ያለው በሩሲያ ሰሜን ካውካሰስ የሚገኝና የሩስያ አካል ከሆኑት 22 ሪፐብሊኮች አንዱ ሪፐብሊክ ግዛቶች አንዱ ሲሆን፣በምዕራብ ከቺቺኒያ እና ከጆርጂያ ጋር ፣በደቡብ ከአዘርባጃን እና በምስራቅ ከካስፒያን ባህር ጋር ይዋሰናል።

የዳግስታን ህዝብ ብዛት 3,209,800 ሲሆን ከ83% በላይ ህዝቦቹ የሱኒ ሙስሊሞች ናቸው።)

▶️የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ የሀማስን የጋዛ ሀላፊ የህያ ሲንዋርን እስከምንገድል ወይንም እስከምንማርክ ድረስ ወደጋዛ ዘልቀን እንገባለን፣በጋዛ ያለውን የሰራዊታችንን እንቅስቃሴም አናሳውቅም ብሏል!

Umma1698005714

Send as a message
Share on my page
Share in the group