Translation is not possible.

በመጀመሪያ ደረጃ በጋዛ ወንድም እና እህቶቻችን ላይ እየደረሰ ባለው በደል እንኳን ሙስሊም የሆነ ቀርቶ ነፃ አእምሮ ያለቸው ሙስሊም ያልሆኑ ሠዎች አዝነዋል። ይሄንንም በተለያየ መንገድ ገልጸዋል። ጥያቄው እነዚህ መንገዶች እስከ የት ድረስ ያደርሰናል የሚለው ነው። ሠላማዊ ሠልፍ ብቻ ወደ የት ያሻግረናል? መንግስታቶቻችን ("ኢስላማዊ የሆኑት" (ባይኖርም)) ግማሹ የእነርሱ ጫማ ላሽ ባሪያ ሲሆኑ የተቀሩት ከቃላት ያለፈ ማድረግ የማይችሉ ናቸው። አሁን ያለው ሁኔታ ቢቆም ትንሽ ቢቆይ ስንቶቻችን "short memory" ሆነን ይሄን በደል እና ግፍ ረስተን መልሠን የእነርሱ ገረድ እና አድናቂ እንሆናለን? ምክንያቱም ይሄ ክስተት ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም እየሆነ ያለው። ስለሆነም ነው የአጭር እና የረጅም ጊዜ መፍትሔ ማመንጨት ግዴታችን የሆነው። ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ ተግባር ግድ የሆነው። ይሄ ነገር የእያንዳንዳችንን ልፋት ጥረት ፈጠራ ይሻል። ፍልስጤሞች በዚያ ፈተና ውስጥ የራሳቸውን መፍትሔ ካመጡ እኛስ? ብናስብበት ይሻላል አለበለዚያ በደሉ..........

Send as a message
Share on my page
Share in the group