7 month Translate
Qumuqta qilghuchi yo'q.

አንድ ዶክተር መድሐኒት እየቀመመ ሳለ ሱልጣን ባያዚድ ባጠገቡ ሲያልፍ እንዲህ በማለት ጠየቀው:-

"ዶክተር ሆይ! ለእኔ በሽታ የሚሆን መድሐኒት ይኖርሀል?"

"የእርስዎ በሽታ ምንድነው?"

"የሀጢአት በሽታ" በማለት መለሰ ባያዚድ።

ዶክተሩ በዚህ ጊዜ እጆቹን ወደላይ አድርጎ እንዲህ አለ:-

"እኔ ኃጢአትን የሚያድን(የሚፈውስ) መድሐኒት አላውቅም።"

በዚያው ቅፅበት ንክ የሚመስል አንድ ወጣት በዚያ ቦታ ላይ ነበርና እንዲህ በማለት መናገር ጀመረ:-

"እኔ ለአንተ በሽታ የሚሆን መድሐኒት አውቃለሁ።" ባያዚድም በደስታ

"እባክህ ንገረኝ አንተ ወጣት!" አለው።

ወጣቱ ኃጢአትን ለማከም የሚያስችለውን ዘዴ እንዲህ በማለት አብራራ:-

"አስር የሚሆኑ የተውባ ዛፍ ስሮችን እንዲሁም አስር የሚሆኑ የእስቲግፋር ቅጠሎችን ያዝ። ከዚያም በልብህ ወፍጮ ውስጥ አስቀምጣቸው። በተውሒድ ዘነዘና ውቀጣቸው። ከዚያም በደግነት ወንፊት ንፋቸው። በእንባህም ለውሳቸው። ከዚያም በፍቅርና በፀፀት ምድጃ ላይ አብስላቸው። ከዚህ መድሐኒት በየቀኑ አምስት ማንኪያ ውሰድ በውስጥህ አንድም በሽታ አይቀርም።"

ባያዚድ ቢስቲመኢ ትረካውን በጉጉት ሲከታተል ከቆየ ቡኋላ በረዥሙ ተንፍሶ እንዲህ አለ:- "እነዚያ እራሳቸውን ጥበበኞችና ጎበዞች አድርገው የሚቆጥሩና አንተን ደሞ እብድ ነው የሚሉ ወዮላቸው!"

Send as a message
Share on my page
Share in the group