ኔታንያሁ እስራኤላውያን ለረጅሙና አስቸጋሪው ጦርነት እንዲዘጋጁ አሳሰቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ዜጎች ለረጅሙ እና አስቸጋሪው ጦርነት እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የእስራኤል ጦር በጋዛ ሃማስ ታጣቂዎች ላይ የሚያካሂደው ወታደራዊ እርምጃ ሁለተኛ ምዕራፍ መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ÷እስራኤላውያን ከፊታቸው ላለው ረጅም ትግል አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሃማስ ጋር እየተደረገ ያለውን ጦርነት የሀገሪቱ ሁለተኛ የነጻነት ጦርነት ነው ሲሉ ገልጸውታል።
በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በሃማስ ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሱ ከፍተኛ የአየር ድብደባዎች መካሄዳቸውን ነው ኔታንያሁ የገለጹት፡፡
የምንገኘው በመንገዱ መጀመሪያ ላይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ በጋዛ ሰርጥ ያለው ጦርነት ከባድ እና ረጅም ይሆናል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን አር ቲ ዘግቧል።
በአንጻሩ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የፍልጤም ደጋፊዎች እስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ በሰላማዊ ሰልፍ እየጠየቁ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
እስካሁን በተካሄደው የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት በጋዛ ከ8 ሺህ በላይ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የፍልስጤም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በሌላ በኩል በአስቸጋሪ ሁኔታው ውስጥ የሚገኙት የጋዛ ነዋሪዎች የእርዳታ መጋዘኖችን ሰብረው በመግባት መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን መውሰዳቸው በዘገባው ተጠቁሟል፡፡
#ummalif#palatine #abdellahali