1 year Translate
Translation is not possible.

اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎

           ሒጃብ ነው ውበትሽ

ሙስሊሟ እህቴ ሆይ - አንዴ ጆሮ ስጭኝ

ላንች የምትጠቅም -ቲንሽ ምክር አለችኝ።

በርግጥ አይጠፋሽም - ይህ ላንች ግልጽ ነው

ግን እንዳትዘነጊው - ላስታውስሽ ብየ ነው።

ይሄውልሽ እህት - ምክሬ እንድህ የሚል ነው

አሏህን ያልፈራ - አደብ የሌለው ሰው

"አይንሽ በጣም ያምራል - የንጋት ኮከብ ነው

ጸጉርሽ ሐር ይመስላል - አንገትሽ ዞማ ነው

ጥርሶችሽ ያምራሉ - የደስደስ አላቸው

ደግሞ ዘበኛውም - ከንፈርሽም ማር ነው

አቦ ደስ ትያለሽ - በጣም ውብ ቆንጂት ነሽ

ለዚህ አረማመድ - ለለጋው ቁመትሽ

ለዞማው አንገትሽ -ለቀጭን ወገብሽ

ለትርንጎው ባትሽ - ሎሜ ተረከዝሽ

ለቀጭን እጆችሽ - ለ አለንጋ ጣቶችሽ

ሒጃብ ምን ሊሆንሽ -መሸፈን ለምንሽ ?

ጅልባብ ብሎ - አልባሳት

ከራስ - እስከመሬት

ጡት አያሳይ- አንገት

የወገብን ቅጥነት - ከውጭ የማያሳይ

የዳሌሽን መጠን - በቅጡ የማያስለይ

እረ ይደብራል - የጅልባብ ስፋቱ

ለውበትሽ ሳይበጅ - በዛው ላይ ሙቀቱ

አትልበሽው አልኩሽ - በቃ ይቅር ተይው

ደግሞ በዚ ሙቀት - የምን መጨነቅ ነው?

ቅርጽሽን የሚያሳይ - ጠበብ ያለ ልበሽ

ባይሆን አጠር ይበል - እንዳያስቸግርሽ

አየርም ተቀበይ - በመላ አካላትሽ ።

እንድህ ነው ቁንጅናሽ -እንድህ ነው ዉበትሽ

ያየሽ ፈዞ ሲቀር - ዝናሽ ሲወራልሽ

ፈላጊሽ ሲበዛ - ሲከበብ ሰፈርሽ

አጃቢሽ ሲበዛ - ከኋላ ከፊትሽ

የአይን ሻውር ሁነሽ - በሃገር መጠራትሽ

እንድህ ነው ቁንጂናሽ - እንድህ ነው ውበትሽ።”

ብሎ የሚመክርሽ - የሰፈር ወጠጤ

ይሁዳ የቀረጸው - አስተሳሰቡ መጤ

ለህይወቱ የማያቅ -ለሰይጣን እጅ የሰጠ

ከ ኢስላም ምህዋር - ወጥቶ ያፈነገጠ

ህሊናውን የሳተ - ልቡ የቀለጠ

በምርቃና ሰምጦ - አይኑ የፈጠጠ

ማስተንተን አቅቶት - ስሜት የሚገዛው

በሱስ ተበርዞ - አላማው የጠፋው

እንኳን ላንች ሊመክር - ለራሱ ጨልሞት

እልቅ እኔን ስሚኝ - አትዘናጊለት።

በውሸት ታፍኖ - አንደበትሽ ሳይዝል

ፈጣሪ ያደለሽ - ማንነትሽ ሳይጎድል

ተከብረሽ ለመኖር - በቁም ላለመሞት

ነገር ሳይበላሽ - አሁን ላይ ነው መንቃት

አድናቂሽ ቢበዛ - በሽወች ቢቆጠር

የወጣቱ መንጋ - በሰፈርሽ ቢዞር

ከፊትሽ ቢመራ - ከኋላሽ ቢከተል

እንደ አሸን ቢፈላ - በዝቶ ቢጉተለተል

ምላሱን ቢያጣጥፍ - ውሸቱን ቢቀምር

ዘንጦ ቢወጣ - ምንም መልኩ ቢያምር

እሽ ያልሽው እለት - ስሜቱን አርክቶ

አንችን ጨለማ ውስጥ - ወንጀል ውስጥ ከቶ

ክብርሽን አጉድፎ - ስምሽን አጥፍቶ

ደበርሽኝ ይልሻል - ልቡ ሌላ አስቦ - ስሜቱ አገርሽቶ

ያንችም እጣ ፈንታ - ግልጽ ነው ታቂያለሽ

ካጠገብሽ ሲርቅ - ያመንሽው ሲከዳሽ

አባብሎ አሙኝቶ - ወንጀል አሰርቶሽ

ጥሎሽ ገለል ሲል - ክብርሽን ቀምቶሽ።

እውነት - በጣም ያማል

ህሊናን - ያቆስላል !!!

የወንጀሉ ክብደት - ሳይደንቀው ሳያፍር

ለሚሰማው ሁሉ - ያወራል በዝርዝር

ዝና እየመሰለው - አይጠብቅም ምስጢር

ከአሏህ ያጣላሽ -ወንጀሉ ሳያንስሽ

በተከበርሽበት - በሰፈሩ አስንቆሽ

ጥሎሽ ዘወር ሲል - ከሚያይል ጸጸትሽ

ከነዳማ ክምር - ከማታርፊው ወቅተሽ

ብትሰሚኝ ጥሩ ነው - እህቴ ልምከርሽ

ሒጃቡን ልበሽው - መስፈርቱን ጠብቀሽ

ተትረፍርፎ ይውረድ - መሬት ላይ ይጎተት

ጎኑም እንዳይጠብሽ - ይሰራ በስፋት

የሳሳም እንዳይሆን - አውረትን የሚያሳይ

ከለሩም ይደብዝዝ - እንዳይሆን አማላይ

ጽዳቱም ይጠበቅ - ይያዝ በጽሞና

የሙስሊምነት አርማሽ - መለያሽ ነውና።

የክብርያሽ ምንጩ - ታይተሽ መታፈሪያሽ

በዱኒያ በአኺራ - በኸይር መጠሪያሽ

ስትሸፈኝ እንጅ - አይደለም ተጋልጠሽ

ጠበቅ አድርገሽ ያዢ - ሒጃብ ነው ውበትሽ።

ለመከርኩሽ ምክር - "ማስረጃውን?" ካልሽኝ

በ ሱረቱል አህዛብ - አንቀጽ ሃምሳ ዘጠኝ

በግልጽ ተቀምጧል - አልዋሽም እመኒኝ።

ከአመታት በፊት የተጻፈ

اَوَّل بِن نُورُ(اب عمران)

Send as a message
Share on my page
Share in the group