Translation is not possible.

ፖለቲካ ያለመርህ ከራስ ጥቅም ጋር ብቻ ሲሰላ - ባለሁለት ስለት ቢላ /

"HYPOCRISY"

~~~~~~~~~~

___የአቅል አይምሮ ትዝብት

.

ትልቅ ቦታ ተሰጥቶት ትልቅ ነገር የሚጠበቅበት ሰው ያለቦታው ሲገኝ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ብዙ የአለማችን የፖለቲካ ሰዎች እዉነተኛ የዉስጥ ባህሪ ዉሸት ፣ሸፍጥና አምባገነንነት ነው፡፡ ለዚህም ነው ህዝብ ንቁ ሆኖ በህብረትና በተቋማቶች ታግዞ ክትትል የሚያደርግ ብሎም እግር ከእግር የሚከታተል ጠያቂ ካልሆነ በቀር የፖለቲከኞች መጫወቻ ነው የሚባለው፡፡ ለምን ቢሉ መንግስታትና ፖለቲከኞች መለጎምያ ህግና ያሉትን ሁሉ በጭፍን ሰምቶ የሚከተል ሳይሆን መርህ ያለውን መስመር የሚከተል ጠያቂ ህዝብ ከሌለባቸው በቀር በባህሪያቸው አምባገነኖችና ወደ መጨቆን የሚያደላ ተፈጥሯዊ ባህሪ ስላላቸው ነው፡፡

.

ይህ በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ባለፈው ሰሞን በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢራኑ ሰው ንግግር ለማድረግ በሚዘጋጁበት ወቅት "የኢራን ሴቶች ነጻነት ይገባቸዋል!" የሚልን መፈክር አንግቦ ተናጋሪዉን በማወክ በጸጥታ አስከባሪዎች ከአዳራሹ እስኪባረር ድረስ ለያዥና ገናዥ አስቸግሮ ነበር፡፡

.

ዛሬ ስለፍልስጤም ሴቶች ቀርቶ ስለህጻናቱ እንኳን ቢጠየቅ "ምን ጎደለባቸው፣ እንደዉም ሲበዛባቸው ነው!" የሚል አቋም እንደሚያራምድ ሲታሰብ የአለም ህዝብ የማገናዘብ አቅምን የናቀ ከማለት ዉጭ ምን ሊባል ይችላል?

.

ይኸው ምሳሌ ነው እንግዲህ እንደ ጀርመንና ፈረንሳይ ባሉ ሃገራት የሃሳብ ነጻነትን አዉጀው ሲያበቁ ለእስራኤሎች መሰልፍን ፈቅደው ለፍልስጤም ደጋፊዎች መከልከል፣ ማስፈራራትና ብሎም እርምጃ መዉሰድ የገቡት! ለዚህም ነው አሜሪካ እና አጋሮቿ ለዩክራይን እራስን የመከላከል መብቷን አዉጀው፣ ስለሰባዊ መብት እያወሩ ቁጥር አልባ ድጋፋቸዉን እያፈሰሱ ሩስያን ደግሞ ወራሪ፣ ተስፋፊ፣ የሰው መሬት ናፋቂ ፣ጨፍጫፊ፣ አምባገነንና ጭራቅ አድርገው የሳሉት፡፡

.

በሌላ በኩል ለፍልስጤም ጊዜ ሲሆን ፍልስጤምን ሩስያ ፣ እስራኤልን ደግሞ ዩክራይን አድርገው የገለበጡት!

.

ፖለቲካ ያለመርህ - ማለት ይሄም አይደል?! "HYPOCRISY" እንዲል ፈረንጁ!

.

እ! ምን አላችሁ? - ጻፉና እስኪ እናንብባችሁ!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group