Translation is not possible.
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጀበ ጠይብ ኤርዶጋን ዛሬ ምን አለ ?
 
#palestine ዛሬ በኤርዶጋን መሪነት በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በኢስታንቡል ከትሞ ለፍልስጤማውያን ያለውን አጋርነት ሲያሳይ ነው የዋለው !
ኤርዶጋን ዛሬ በኢስታንቡል አደባባይ ህዝብ ያስተላለፈው መልእክት ከወትሮው በጣም የጠነከረ ነው ። ከኤርዶጋን ንግግሮች
 
፨ ፍልስጤሞች ስለ ክብርና ነፃነታቸው እየተዋደቁ ነው እኛስ ዝግጁ ነን ወይ ?
 
፨ እስራኤል ሆይ አንቺ አሸባሪ ሀገር ነሽ አንቺ አሸባሪ ድርጅት ነሽ !
 
፨ በህይወቴ ከሚፀፅተኝ ነገሮች አንዱ ቤንጃሚን ኔታኒያሁ የሚባል አረመኔ እጅ የጨበጥኩባት አንድት ቀን ናት !
 
፨ ሀማስ የነፃነት ታጋይ ነው አሸባሪዋ ወራሪዋ እስራኤል ናት !
 
፨ እስራኤልን አረመኔነቷን የጦር ወንጀለኝነቷን ለመታገል ወስንናል !
 
ከዛሬው የኤርዶጋን ንግግር በሗላ እስራኤል ሁሉንም ድፕሎማቶቿን ከቱርክ ጠርታለች ። ሁለቱ ሀገራት የቃላት ጦርነት ላይ ናቸው ።
 
ቱርክ በቀጣይ ምን ልታደርግ ትችላለች ? አብረን የምናየው ነው ።
ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ትፈፅማለች ተብሎ ግን አይጠበቅም ከአሜሪካ ጋር በቀጥታ የሚያላትማት ነውና !
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group