Tarjima qilib boʻlmadi.

"ቂያማ" የሚባል እለት ስለመኖሩ አላህን ልክ የሌለው ምስጋና አመሰግነዋለሁ። ይህ የፍትህ ቀን ባይኖር የተባዳይን የሀዘን እና አቁጭት ንዳድ ምን ያበርድለት ነበር!

ዛሬ ላይ በኢምንት ሀይላቸው ተመክተው ህፃናትን እንደ ትንኝ የሚያራግፉ ሀያላን መሪዎችን አላህ ፊት እጅ እግራቸው ተጠፍልጎ ክስ ሲነበብላቸው እንደማየት አንጀት የሚያርስ ነገር ምን አለ!

ዛሬ ላይ በጭካኔ ተሞልተው በህፃናት እሳት የሚያዘንቡ በዳዮችን፤ ነገ በቂያማ አይኖቻቸው ታውሮ እጅ እግራቸው ታስሮ በመላዕክት እየተጎተቱ ወደ ፍርዱ ስፍራ ተዋራጅ ሁነው ሲሄዱ ማየት ምንኛ ያራካል!

በማን አለብኝነት "የአለም ሀያል ነኝ" በሚል መንፈስ ያለ ከልካይ ጦሩን ልኮ የፊለስጢንን ህፃናት የሚያስፈጀውን ባይደንን መላዕክት እርቃኑን አሳስረው ከጀሀነም ሸለቆ ውስጥ ሲወረውሩት እንደማየት ሚያስደስት ምን ትዕይንት አለ!?

image
image
image
Xabar sifatida yuborish
Sahifamda baham ko'rish
Guruhda ulashish