የሕክምና ተማሪ ነው። ከሚማርበት ኮሌጅ ፊት ለፊት ከጓደኞቹ ጋር ቆሞ በመልካም ነገር ይተዋወሱ ይዘዋል። አላህን የሚፈሩ ሷሊህ ጓደኛሞች ናቸው። በድንገት ሲበር ከፊትለፊቱ በመጣ መኪና ተገጭቶ መሬት ተዘረረ። ደሙ ያለማቋረጥ እየፈሰሰ ከመሬት ተዘረረ። እሱን ብቻ ነጥሎ አጋደመው። አፋፍሰው ወደ ሆስፒታል ይዘውት ሄዱ። የቀኝ ኩላሊቱ እየደማ ነበር። ዶክተሮቹ ከኩላሊቱ አሊያም ከነፍሱ አንዱን መምረጥ ግዴታቸው ስለነበር በአላህ ፈቃድ ህይወቱን ታደጉለት።
ከሀያ ሁለት ቀናት በኋላ በክፍሉ አልጋ ላይ እንደተጋደመ ቀዶ ጥገና ያደረገለት ዶክተር ወደተኛበት አልጋ ፈገግ ብሎ ተጠጋ፡-
"ስለቀደር ምን ያህል ሰምተሀል?" ሲል ጠየቀው።
"ብዙ ጊዜ ሲወራ ሰምቻለሁ ከመጽሐፍቶችም ላይ አንብቤያለሁ" ሲል መለሰ።
ዶክተሩ ፀጉሮቹን እያሻሸ "ባንተ ላይ እስካየው ድረስ እኔም ስሰማው ኖሬያለሁ። የሆነውን ልንገርህማ ቀዶ ጥገናውን እያደረኩ ሳለ ኩላሊትህ ላይ እንግዳ የሆነ ነገርን አስተዋልኩ። ናሙናው ለምርመራ ወደ ላብራቶሪ ተላከ። ውጤቱ ሲመጣ በአላህ ስራ በእጅጉ ተገረምኩ። በጣም ዘግይቶ ሊታወቅ የሚችልና በፍጥነት ገዳይ የሆነ የካንሰር ምልክት በኩላሊትህ ላይ ተገኘ። በእርግጥም የመጀመርያ ደረጃ ላይ ያለና በቀላሉ የሚድን ቢሆንም አደጋው የህይወትህ ዋጋ ነበር የካንሰር በሽታው ኩላሊትህ ላይ ነበር" አለና ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።
ተማሪው ዶክተሩን እየተመለከተ
"መኪናው እኔን ብቻ መርጦ የገጨኝ የካንሰር በሽታው ሰውነቴ ውስጥ ሳይዛመት በፊት አንዱን ኩላሊቴን አጥቼ በቀላሉ ከካንሰር ድኜ በህይወት እንድኖር ሁለተኛ ዕድል አላህ ሊሰጠኝ ፈልጎ ነው ማለት ነው?!" አለ።
ዶክተሩ ከዓይኑ ላይ ዕንባውን እየጠራረገ "ታዲያ የጌታህ መድኃኒት በድንገትና በአጋጣሚ የተከሰተ ይመስልሀልን?!" ሲል ጠየቀ። ተማሪው በፈገግታ "በእርግጥም ይህ ነው ቀዳእና ቀደር" እያለ አላህን ደጋግሞ አመሰገነ።
Copy