Translation is not possible.

እስራኤል 680 የጦር ጄቶች አሏት ።

ሁሉም በሚባል መልኩ አሜሪካ ስርታ ያስረከበቻት ነው ።

ከነዚህ ውስጥ 360 የሚሆኑት ሀያሎቹ የአሜሪካ F-16 የጦር ጄቶች ናቸው !

36 የሚሆኑት ደግሞ ከራዳር እይታ ውጭ መብረር የሚችሉትና የየትኛውንም ሀገር ድንበር ጥሰው ሲገቡ የማይታዩት F-35 የጦር ጀቶች ናቸው ። ሁሉም አሜሪካ ሰራሽ ናቸው !

በዚያ ላይ 2,200 ታንኮች አሏት አብዛኛው ከአሜሪካ የተገኙ ናቸው ።

አሜሪካ እስራኤልን ከሀማስ ትከላከልበት ዘንዳ Iron dome የተሰኘውን የአየር መከላከያም አስታጥቃለች ።

እስራኤል ከ 500,000 በላይ እግረኛ ጦርም አላት ።

ወታደራዊ በጀቷ 24 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 4 ቢሊዮን ዶላሩ በአሜሪካ ይሸፈናል ።

ፍልስጤማዊያን የሚታገሉት ከዚህች የአሜሪካና የእንግሊዝ ልጅ ጋር ነው ።

እስራኤልን ማጥቃትም ሆነ መደብደብ ለኢራንም ሆነ ለሌሎች የእስራኤል ጠላቶች በጣም የሚያስፈራ ሆኖ አይደለም ። ዋናው ፈተና አሜሪካ ከጀርባ መሰለፏ ነው ።

ጠላት ሀያል ነው ተብሎ ሙቶ አይጠበቅምና ፍልስጤማዊያን በፅናት እየታገሉ ነው ። ይሄው ለ 22 ቀን ገትረው ይዘዋታል ። ባለቤቷን የተማመነች በግ እንዲሉ እስራኤልም ጌታዋን አሜሪካን ተማምና በእብሪቷ ቀጥላለች !

ፍልስጤሞችም አላህን ቢሞቱ ውደታውን ቢኖሩ ድሉን አምነው እየተዋደቁ ነው !

Send as a message
Share on my page
Share in the group