Translation is not possible.

እዚህጋ ደሞ ሌላ ትኩሳት ከወደ ( አፋር)

ሼር በማድረግ ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ ተባበሩን 🙏🙏🙏

👉አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ከአፋር ህዝብ

ለክቡር ዶ/ር Abiy Ahmed Ali

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነት እና ለኢትጵያ ሰበአዊ መብት ኮሚሽን እንዲሁም ለሚመለከታችሁ የህዝብ አገልግሎት ተቋማት እንዲሁም ለህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

እንደምታወቀው ልማት ወዳዱ እንዲሁም ከመንግስት ጎን መሆኑን በተደጋጋሚ ያስመሰከረው የአፋር ህዝብ 👇👇

ዘርፈ-ብዙ አገራዊ መሰዋትነት የከፈለ አሁንም ለመክፈልና ኢትዮጵያን ላለማስደፈር ዉድ ልጆቹን የገበረ ፤ ከሀብት ንብረቱንም የተራቆተ ብዙ ብዙ ነገር ያጣ ህዝብ ነው

ለ ክቡር ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ያለውን ድጋፍ በአደባባይ ያስመሰከረ ህዝብ ነው👇👇

ይሁን እንጂ ታዳ ይህ የዋሁና አገር ወዳዱ የአፋር ህዝብ ዛሬ ላይ በክቡር ጠ/ሚ/ር ዶ/ር #አብይ እና በብልፅግና ፓርቲ ላይ የነበረው ተስፋ ተሟጦ ልያልቅ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሶ ይገኛል😭😭

በአሁኑ ሰአት በአፋር ክልል ያለው አሰራር ከዘመነ-ወያኔ በላይ አፋኝ፣ አሳሪ፤ አሳዳጅና ፀረ-ዲሞክራሲ ነው ለማለት ተገደናል

የአፋር ህዝብ አሁንም ሠላሙ አልተረጋገጠም!

የአፋር ህዝብ የሴሜኑ ጦርነት ካስተከተለበት መሪር ሀዘን፤ የስነልቦና ቀውስና ከሀብት መራቆት መልሶ ልያገግም ቀርቶ

በአንዳንድ አከባቢ ቤታቸው በጁንታ ተቃጥሎባቸው እስካሁን በዛፍ ስር የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍል መኖራቸው ለከፋ የስነ-ልቦና ቀውስ ዳርጓቸዋል

የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አልተመለሰም የተደራጀ የሙስና ኔትወርክ ተጠናክሮ ቀጥሏል"

ለወጣቱ የስራ እድል መፍጠሩ ይቅርና 👇

በፌስቡክ ላይ ፅፋችኋል በሚል ተልካሻ ምክንያት 👉ሲቪል-ሰርቫንቶችን ከስራ ገበታ እያሰናበቱ የስራ-አጥ ወጣቶች ቁጥር እንዲያሻቅብ ከማድረግ በተጨማሪ ወጣቶች በጅምላ #እያሰሩና ያለፍርድ ዉሳኔ በጊዜ ቀጠሮ #ከአራት እስከ #ስድስት ወር ድረስ በማሰር ወጣቱን ለሁለንተናዊ ቀውስ እያደረጉ ይገኛሉ

👉ብልሹ አሰራር ተጠናክሯል የጨው መሬት ቅሪምቱም እንደቀጠለ ነው ከላይ እስከ ታች በአንድ ኔትዎክ በዉስን ባለስልጣናትና የጥቅም አጋሶቻቸው #በሞኖፖል ተይዞ የአፋር ህዝብ ከሀብቱ የበይ ተመልካች እንዲሆን ተገዷል

👉 የህግ ተጠያቂነት ያለው አሠራር ደብዛው ጠፍቷል

ግልጽነት የጎደለው በግለሰቦች ፋላጎት፣ በጥቅም ትስስር ፣ በጎሰኝነት የሚደረግ፣ መርህ አልባ የሹመት አሰጣጥ፤ ፍትሀዊነት የሌለው የሀብት ክፍፍልና 👉የሙስና ቅሌት በአፋር ክልል ላይ ህጋዊና የብልፅግና ፓርቲ ማኔፌስቶ እስኪመስል ድረስ ሌብነቱ ተስፋፍቶና ተጠናክሮ ቀጥሏል

ስለዚህ የፌዴራል መንግሥቱ በአስቸኳይ እንዲደርስልን ስንል በተራበ አንጀታችን እንጠይቃለን 🙏🙏

( Salah A Muhammad )...✍️

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group