Translation is not possible.

እኔ ፍልስጤማዊያን እጆግ የሚደንቀኝ ጀግንነታቸው አይደለም ! ማንም ጀግና ሊሆን ይችላል!

እኔ ከነርሱ እጅግ ድንቅ የሚለኝ ሶብራቸው ነው ፅናታቸው ! የእነርሱን ፅናት ማንም ህዝብ ላይ አይቼውም አላውቅም !

ቤተሰባቸው አልቀው ፅኑ ናቸው ሶብረኛ ! አካላቸው ጎድሎ እግራቸው እጃቸው ተቆርጦ አይናቸው ጠፍቶ ተስፋ ቆርጠው አይቀመጡም ! ይወጣሉ ይፋለማሉ ይታገላሉ ! ተስፋ አይቆርጡም አይደክሙም አይዝሉም ልባቸው ተሰብሮ አይልፈሰፈሱም ! መላው ምእራባዊ ሀገር ጠላታቸው ሆኖ አያለቃቅሱም ! ታግለው ቢችሉ ጥለው ይወድቃሉ እንጅ ተነፋርቀው ጠላቶቻቼውን አያስደስቱም !

ይሄ ጀግና የአልጀዚራ ጋዜጠኛ ዋኢል አልደህዱህ የፍልስጤማውያን ፅናትና ሶብር አንዱ ማሳያ ነው ።

ትላንት መላ ቤተሰቡን አጣ ልጆቹን የልጅ ልጆቹን ባለቤቱን ተነጠቀ ። ቤተሰቦቹን ራሱ ሶላተል ጀናዛ ኢማም ሁኖ አሰግዶ ቀበረ ። ከዚያስ ከዚያማ ህዝቡ ትግል ላይ ነውና የቤተሰቦቹን ሀዘን ተቀምጦ ከማዘን ይልቅ ወደ ስራ ገበታው ተመለሰ ።

ታድያ ፍልስጤማዊያን የእርሱን ድምፅ በሚፈልጉበት ሰአት እንደት ለሀዘን ይቀመጥ ! በየደቂቃው ቦምብ ከሰማይ በሚወርድባት ጋዛ ከተማ ቁጭ ብሎ ስራውን እየሰራ ይገኛል።

ይሄንን ከፍልስጥኤማውያን ውጭ ማንም ያደርገው አይመስለኝም ! 💔🇵🇸

በመጨረሻም ተንታኞች ጋዜጠኛውን ካዩ በሗላ ያሉትን ልንገራችሁ " እነዚህን ህዝቦች ማሸነፍ አይቻልም።"

ከወንድም ሳዳም

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group