Translation is not possible.
#ተወኩል( በአላህ_ብቻ_መመካት )
 
እየሆነ ባለዉም በሚሆነዉ ነገርም አላህን ማመስገን
,
,
የኢማን ጥንካሬ ከሚፈጥሩት ዉስጥ በጣም ዋነኛዉና ቀዳሚዉ ተወኩል ነዉ።
ተወኩል፦ በሽታ ከሚቆረጥመዉ ጉልበት፤ እርጂና ከሚያደርቀዉ ወጣትነት፤አደጋ
ከሚያወድመዉ ሀብት፤ ሞት ከሚበትነዉ ቤተሰብ፤ ሳይፈልጉት ከሚገለባበጠዉ
የስልጣን ወንበር፤ ከማያስተማምነዉ ጤንነት፤ጠብቀን ከማናቆየዉ ሰላም፤
ከስንዝር እዉቀታችን፤ አላህን ብቻ መመኪያና መኩሪያ ማድረጋችን
አይበልጥም???
,
በዉስጣችን የተወኩል አቅም ስለምናጣ ስጋቶች በቀላሉ
ይቆጣጠሩናል፤አጥብቀን የምንፈልገዉ ነገር ካልተሳካልን እብደት እንኳን ሳይቀር
እጁን ይዘረጋብናል፤ ነገሮች እንቢ ሲሉን መንገድ ቀይሮ ለመሞከር ጉልበት
ያንሰናል። በሌላ በኩል ሸሽቶ ማምለጥ ሲቻል ተቀምጦ መያዝ፤ ሰርቶ ማግኘት
ሲቻል በስንፍና መቸገር፤ተዋግቶ ማሸነፍ ሲቻል እጂን መስጠት፤ ታክሞ መዳን
ሲቻል እንቢ ብሎ መሞት ተወኩል አይደለም። ይህን አይነት ተወኩል ሸሪአዉ
አላስተማረንም፤አእምሮም አላዘዘንም፤ከተጨባጩም አለም ጋር ይፋለሳል። ይህ
ተወኩል ከተባለ ነብዩ በሂጅራ ጉዟቸዉ ላይ ስዉር ዋሻ ዉስጥ ከቁረይሾች አይን
ራሳቸዉን መሰወራቸዉ ለምን አስፈለገ??? መንገድ የሚመራቸዉ ደላላስ
መከራየታቸዉ ለምን ይሆን? በበድርና በእሁድ ከጠላቶቻቸዉ ጋር መዋጋት ምን
ያደርግላቸዉ ነበር? ተወኩል ስለሚያንሳቸዉ ነዉን?????
,
በፍፁም ነገር ግን ተወኩል ጥረትና ትግል በጋራ አብሮ የሚሄድ ልብ ላይ ያለ
ቁርጠኛ እምነት ስለ ሆነ ነዉ።
,
አርሶ ዝናብን፤ መድሀኒት ወስዶ ፈዉስን፤ ለፍቶና ጥሮ ዉጤትን..... መጠበቅ ነዉ
ተወኩል ማለት። በሌላ በኩል ያለ ተወኩል በጥረት ብቻ ማመን ወንጀልና ክስረት
መሆኑ የሚያሻማ ነገር አይደለም። አላህ ስለ ተወኩል በቁርአን ዉስጥ እንዲህ
ይላል፦
,
ምእመናንም እንደሆናቹህ በአላህ ላይ ተመኩ (አል-ማኢዳህ፡23)
,... ቁርጥ ሀሳብም ባደረገህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ። አላህ በርሱ ተመኪዎችን
ይወዳል።(አል-ዒምራን፡152)
, በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰዉ፥ እርሱ በቂዉ ነዉ፤ አላህ ፍቃዱን አድራሽ ነዉ፤
አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ግዜን በርግጥ አድርጓል(አጥ-ጦላቅ፡3)
,
፨ከማንም በላይ በአላህ ላይ የሚመኩት ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ስለ ተወኩል
የሚከተለዉን ብለዋል፦
, ህዝቦች በአንዳች ነገር አንተን ሊጠቅሙህ አስበዉ ቢሰበሰቡ አላህ ለአንተ
የፃፈልህን አንዳች ነገር ያህል እንጂ ሊጠቅሙህ አይችሉም። አንዳች ነገር
ሊጎዱህ አስበዉ ቢሰበሰቡ እንኳን አላህ በአንተ ላይ የፃፈብህን ያህል እንጂ
አይጎዱህም(ቲርሚዚ)
,
ሌላኛዉ የኢማንን ጥንካሬ ከሚፈጥሩት ዉስጥ በሆነዉም በሚሆነዉም ነገር
አላህን አመስጋኝ መሆን ነዉ።
,
ጤንነት በበሽታ፤ ሰላም በጦርነት፤ ሀብት በድህነት ሲተካ፤አይን ሲጠፋ፤ እግር
ሲቆረጥ፤ ቤተሰብ ሲበተን፤ ያን ጊዜ ታላቅ ፀጋ እንደነበሩ ካጣናቸዉ ቡሀላ
እናዉቃቸዋለን።
,
በእጃችን ይዘናቸዉ ግን እንዘነጋቸዉና አላህን ማመስገን እንረሳለን። እኛ ዘንድ
ያሉትን የአላህን ፀጋዎች ቆጥረን አንዘልቅም። የአላህን ፀጋ እያለን በማመስገን
እዉቅና ካልሰጠን አላህ የሰጠንን ፀጋ ነጥቆን እንድናዉቀዉ ከማድረጉ በፊት
ብናመሰግነዉ በምስጋናችን ተጠቃሚዎቹ እኛዉ እራሳችን ነን።
,
አላህ ሆይ ለፀጋህ እዉቅና የሚሰጥ አእምሮ፤ የምትደሰት ልብ፤ የምታመሰግን
ምላስ በአለም ላይ በመጣዉ ወረርሽኝ ነጃ የምንወጣበትን አቅም ስጠን ያረብ
አስታዉሱኝ አስታውሳቹሀለሁና ለኔም አመስግኑ አትካዱኝም(አል-በቀራህ፡152)
Send as a message
Share on my page
Share in the group