Translation is not possible.

ግብፅ ሀይሏን እያሳየች ነው

ከበድ ያለ ወታደራዊ ልምምድን ያሳየችው ግብፅ ጉዳዩ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው ቢባልም አልሲሲ "የግብፅን ደህንነት ለማስጠበቅ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

እስራኤል በጋዛ እያደረገች ያለውን ድብደባ የተቃወሙት አልሲሲ በሰናይ በር ከፍተው ለፍልስጤማውያን እርዳታን እያደረሱም ነው።

እስራኤልን በአራት ደረጃወች ቀድማ በአለም የወታደራዊ አቅም ደረጃ የተቀመጠችው ግብፅ ጦርነቱ ከጋዛ ወቶ ከተዛመተ ምናልባት ከእስራኤል ጋር የመፋለም እድሏ የሰፋ ይመስላል። የመጀመሪያ አቅራረባቸው ለስለስ ብሎ የነበረው አልሲሲ የጋዛን መደብደብ እና እልቂት ከተመለከቱ ወዲህ የንግግር ይዘታቸው እስራኤልን ወደ መኮነን ማዘንበሉም ታይቶዋል። የአሁኑዋ ግብፅ በበርካታ ዘርፎች ከእስራኤል የተሻለ ወታደራዊ አቋም ላይ ናት የሚሉት ተንታኞቹ በስድስት ቀኑ የእስራኤል እና አረብ ጦርነት የደረሰባት ሽንፈትን በዚህ ሰአት የማታስተናግድ አገር ሆናለች ሲሉ የአለም አገራት አጠቃላይ ወታደራዊ አቋም አጥኝወች ይናገራሉ።

እስራኤል የአየር የበላይነት እንዳላት ቢታወቅም ግብፅ ባለፉት ሀያ አመታት ከፍተኛ የሚባል የአየር ሀይል አቋምን ይዛለች።

በመሬት ቆዳ ስፋት በህዝብ ብዛት እንዲሁም በተጠባባቂ ወታደራዊ ብዛት ቁጥር ግብፅ የበላይነቱን ትይዛለች።

ግብፅ እና እስራኤል ያላቸው ግንኙነት በቅርብ አመታት በጥቂቱም ቢሆን መሻሻል በማሳየቱ ወደ ጦርነት አይገቡም እያሉ ያሉ ቢኖሩም አልሲሲ ለአዲስ ፕረዘዳንታዊ ምርጫ ሲሉ ስህተት እንዳይሰሩ ሲሉ የሚጠራጠሩ አሉ።

ግብፅ በዚህ በማይጠበቅ ሰአት የወታደራዊ ጡንቻውን ለማሳየት ለምን ፈለገች የሚለውም መልስ አልተገኘለትም ቴላቪቭ እና ካይሮ አንዴ ቀዝቀዝ ሌላ ጊዜ ለብ ያለ በሚመስል ግንኙነታቸው በሰና በርሀ ድንበር ተጋርተው የሚኖሩ በመሀከለኛው ምስራቅ ኤሽያ በወታደራዊ አቅም ጠንካራ የሚባሉ አገራትም ናቸው።

ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት የእስራኤል አየር ሀይል ጋዛን በማጥቃት ሂደት ውስጥ በተፈጠረ ስህተት ነው በሚል የግብፅ ግዛትን መምታቱ ተሰምቶዋል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group