Translation is not possible.

🔶ሸሪዓዊ ህክምና 3🔶

ጅብሪል (عليه السَّلامُ) ለነቢዮ ሩቂያ ያደርግላቸው ነበር!

ከአቡ ሰዒድ አልሁድሪ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ:  እንዲህ ይላል፦

﴿أنّ جِبْرِيلَ، أتى النبيَّ ﷺ فَقالَ: يا مُحَمَّدُ اشْتَكَيْتَ؟ فَقالَ: نَعَمْ قالَ: باسْمِ اللهِ أرْقِيكَ، مِن كُلِّ شيءٍ يُؤْذِيكَ، مِن شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ، أوْ عَيْنِ حاسِدٍ، اللهُ يَشْفِيكَ باسْمِ اللهِ أرْقِيكَ..﴾

“ጅብሪል መጣና ለነቢዩ (ﷺ) አላቸው:  አንተ ሙሃመድ ሆይ!  አሞሃል እንዴ? ‘አዎ’ አሉት ነቢዩ። ከዛ እንዲህ ብሎ ሩቂያ (ዱአ) አደረገላቸው፦‘ከሚያሰቃይህ በሽታ ሁሉ ከምቀኛ ነፍስና አይን ሁሉ ክፋት በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ። አላህ ይፈውስህ። በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ።’”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2186

Send as a message
Share on my page
Share in the group