Translation is not possible.

አስተማሪ ስለሆነ እርስዎ ጋር ብቻ እንዲቀር አያድርጉ ለሌሎች ያስተላልፉ

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መስጂድ ለመሄድ በሚጠቀሙት መንገድ ላይ ጠብቃ ቆሻሻ የምትወረውርባቸው አንድ አዛውንት ነበረች::

ነብያችን በየቀኑ ወደ መስጂድ ሲመላለሱ እየጠበቀች ቆሻሻውን ትደፋባቸዋለች"

እርሳቸውም ግን ችለውት በዝምታ ምንም አይነት መቆጣትን ሳያሳዩ ያልፋሉ::

ይህ የተለመደ ክስተት ሆኗል ። አንድ ቀን የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በመንገዱ ሲያልፉ እንደ ወትሮው ቆሻሻ የምትደፋባቸው ሴትዮ የለችም" ።

ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) በቦታው ላይ ቆመው ስለ ጤንነቷ ጎረቤቷን ጠየቁ።

የሴትየዋ ጎረቤትም አዛውንትዋ ታማ አልጋ ላይ እንደተኛች ነገሯቸው::

የአላህ መልዕክተኛም (ሰ.ዐ.ወ) ወደ አዛውንቷ ቤት መግባት እንደሚችሉ በትህትና በመጠየቅ ሲፈቀድላቸው ገቡ። "

ሴትየዋ ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ)ን ስትመለከት ለበቀል እንደመጡ

በማሰብ አቅሜ ሲደክም በሽታ አልጋ ላይ ሲያስተኛኝ ልትበቀልኝ መጣህ? አለቻቸው።

"እርሳቸውም የመጡት ለበቀል ሳይሆን

መታመማቸውን በመስማታቸው አዝነው ሊጠይቋትና የምትፈልገው ነገር

ካለ ሊያሟሉ ፍቃደኛ መሆናቸውን ገለፁላት::

አዛውንቷ ከመገረሟ የተነሳ መናገር አቃታት። በአትኩሮት ትመለከታቸው ጀመር::

"ከዝያም እንዲህ አለች አንተ "እውነተኛ የአላህ መልዕክተኛ መሆንህንና አላህም ጌታ መሆኑን እመሰክራለሁ:: በማለት እስልምናን ተቀበለች::

ሱብሃነላህ!!

እንዲህ ነበሩ ነብያችን እጅግ በጣም አዛኝ ተፈቃሪ እና አዛውንት ህፃን

ሳይሉ ሁሉንም በቸርነት የሚያስተናግዱ ምርጥ ነብይ!!! ወላጆቼ ነፍሴ

ቤዛ ይሁንሎት

እባክዎን አስተማሪ ስለሆነ አንብበው ሲጨርሱ እርስዎ ጋር ብቻ እንዲቀር አያድርጉ ለሌሎች ያስተላልፉ ሼር

Send as a message
Share on my page
Share in the group