Translation is not possible.

ትውልደ እስራኤላዊት ናት። ቤቷ ዘልቀው የነበሩትን የቀሳም ሙጃሂዶች ገጠመኝ በአንደበቷ እንዲህ ስትል ታወጋናለች:-

  "ቀሳም የሚል ፅሑፍ የሰፈረበት አረንጓዴ ጨርቅ ግንባራቸው ላይ ያሰሩ ታጣቂዎች ወደ ቤቴ ዘለቁ። አለባበሳቸው ያስፈራል። ፊታቸውን በጭምብል ሸፍነዋል። ሳያቸው በድንጋጤ ተውጬ የሁለት ልጆች እናት ነኝ አልኳቸው እንግሊዘኛን ተጠቅሜ።

ከመሐላቸው የሚገኘው ጋንታ መሪ ትኩር ብሎ ተመለከተኝና "እኛ ሙስሊሞች ነን በንፁሐን ላይ ድንበር አናልፍምና አትፍሪ" አለኝ። በመልሱ ተገረምኩ። በፍርሀት እንደተዋጥኩ ልጆቼን ጭምቅ አድርጌ አቀፍኩ። ጠረጴዛ ላይ ሙዝ አየና ጠየቀኝ። "አንድ ፍሬ እንድመገብ ትፈቅጂልኛለሽን?" አለኝ። ተመገብ ለጓደኞችህም ስጣቸው አልኩት በስርአታቸው እየተገረምኩ። ለሁለት ሰአታት ቤቴ ተቀምጠው በሩን ከውጪ ዘግተው ወጡ።

እኔ ድንበር ባለፉባቸው ሰዎች ላይ ሙጃሂዶቹ ባሳዩት ኢስላማዊ ስነምግባር ተደንቄያለሁ!! ዘገባው የአልጀዚራ ነው

Send as a message
Share on my page
Share in the group