Translation is not possible.

እፈልጋችኋለው ......

ሰሞኑን ኢትዮ ላይ ራሳቸውን አጠፉ የሚባሉት ወጣቶች ተደጋገሙብኝና ጫር ላድርግ ብዬ ነው። ያው ጉዳዩ ራስን ማጥፋት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ከበድ ይላል። ግን እስኪ ለያይተን እንመልከተው።

ጉዳዩ:- ምክኒያትና ውጤት ያለው ነገር ነው።

ምክኒያቱ :- depression (ድብርት)

ውጤቱ :- ራስን ማጥፋት

ነገር ግን ትንሽ ነገር ማለት የምፈልገው ስለ ምክኒያቱ ነው። ብዙ ጊዜ የሆነ ሰው ስናገኝ እንዴት ነህ?! ቤት ገዛህ?! አገባህ?! ወይም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ነው የምንጠይቀው ነገር ግን እስኪ ደስተኛ ነህ?! ወይም ደስተኛ ነሽ?! ብለን ጠይቀናቸው እናውቃለን? በጭራሽ አናውቅም። ሲደበሩ ስናያቸው ራሱ ምን ያስደብርሀል ነቃ በል እንጂ እያልን ህመማቸውን እናጣጥልባቸዋለን። depression(ድብርት) እንደምታስቡት ዝም ብሎ ተራ ስሜት አይደለም። ይልቁኑስ ዱንያን ሙሉ በሙሉ ጨለማ እንድትሆን የሚያደርግ የሚያስጠላ ስሜት ነው። እና ሰዎች ይሄ ስሜት ሲሰማቸው ከሚረዳቸው ይልቅ የማይረዳቸው ይበዛል ለዚህም ነው ከመኖር ይልቅ ላለመኖር የሚወስኑት። ነገር ግን ይሄ ሐሳብ ያላቸው ሰዎች ሊያውቁት የሚገባው ነገር ቢኖር አሏህ ሁሉን ነገር ተመልካች እንደሆነና ይሄ ጊዜ እንደሚያልፍ ነው። አዎ ያልፍና ደስተኛ የምትሆኑበት ጊዜ ይመጣል። ከዛ "ለዚህ ነበር ተስፋ ልቆርጥ የነበረው" ብላችሁ ራሳችሁን ትወቅሱታላችሁ።

ራስን ማጥፋት ለምንም አይበጅም። ለሚያጠፋውም የበለጠ ስቃይ ነው የሚጠብቀው። ለቤተሰብም ሐዘን ነው። ነገር ግን አንድ ነገር እወቁ አቡ ተይሚ ይፈልጋችኋል።

እወዳችኋለው አሏህ ረጅም እድሜ ከመልካም ስራ ጋር ይስጠን

ቻናል:- t.me/hafugraphics

t.me/senegruhsema

Send as a message
Share on my page
Share in the group