Translation is not possible.

ምን አድርጌ ይሆን -- አንተን የሚያስቆጣ

በምን ወንጀሌ ነው -- እንዲህ የምቀጣ

ብየ አልጠይቅህም

ችግር ነካኝ ብየ -- ባንተ አላማርርም

አውቃለሁ ወንጀሌን

በግልፅም በሚስጥር -- ሁሌ ምሰራውን

ባንተው እዝነት እንጅ -- ባንተው ሁሉን መቻል

እንደኔማ ቢሆን -- እንደኔማ ወንጀል

እንኳን እንዲህ ልኖር -- ከኔ ምንም ሳይጎል

በወንጀሌ ብዛት -- በኔው ስራ ሰበብ

ድንጋይ ነበር ከላይ -- በኔ ላይ የሚዘንብ

እጄን ከፍ አድርጌ -- እንድል ይቅርበለኝ

ለፈተና ትንሽ -- ህመም ብትነካኝ

ይችው ካቅሜ በልጣ -- መቋቋም አቃተኝ

ግን አልጠይቅህም በምን ጥፋቴ ነው??

-- ብየ ምን አረኩኝ??

እንደው በደፈናው -- እንደው በሽፍኑ

አንተው ይቅር በለኝ -- ጌታየ መናኑ

-------------------

አውቄያለሁ እና --- አቅሜን አሳምሬ

ዓፋ በለኝ እና --- ዓፊያ አድርገኝ ዛሬ

--------------------

አሚን አሏሁመ አሚን

--- --- --- --- ---

ያ አህባቢ አሏህ አፊያየን እንዲሰጠኝ ዱአ አድርጉልኝ

በዛውም follow አድርጉ

Send as a message
Share on my page
Share in the group