ሂጃማ–ዋግምት–cupping።
የነብያችን(ሰላዋቱ ላሂ ወሰላሙ ዐለይሂ) የጥንት የሕክምና ዘዴ።
የዋግምት ህክምና የሰውነት አካል ላይ እንደ ብርጭቆ ወይንም ኩባያ ያለ እቃ በመድፋት እና ቆዳን በመምጠጥ የሚካሄድ ጥንታዊ የባህል ህክምና ዓይነት ሲሆን በጥንት ግብፃዊያን ፣ በቻይናዊያን ፣ በዓረቦች እና በህንዳዊያን እንዲሁም በአገራችን ትልቅ ግምት የሚሰጠው የህክምና አይነት ነው፡፡
በሀገራችን ቀደምት አያቶቻችን በሰፊው የተካኑበት የዋግምት ህክምና በአረቦች፣ በሩቅ ምስራቅ ሀገራትና በተለያዩ ህዝቦች በባህላዊ መልኩ ሲሰራበት የቆየ አማራጭ የህክምና ዘዴ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከቻይና አልፎ አውሮፓና አሜሪካ ሳይቀር በአማራጭ ህክምና ለብዙ ህሙማን ፈውስ በሰፊው ይሰራበታል።
በሀዲስም ነቢዩ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ምርጥ ህክምና መሆኑን ከመምከር አልፈው ራሳቸውም በዋግምት ታክመዋል።
ዋግምት ወይንም ሂጃማ በመባል የሚጠራውን ይህን ህክምና ለመስጠት የሚያገለግሉት ኩባያ መሳይ እቃዎች ከተለያዩ ቁሶች የተሰሩ ሊሆኑ ቢችሉም የተለመዱት ግን ከሸክላ፣ ከሸንበቆ፣ ከቀንድ፣ ከሲልከን ፣ ከብርጭቆ እና ከፕላስቲክ የሚሰሩት ናቸው፡፡
የኩባያዎቹ ብዛት እና የሚቀመጡበት ቦታ እንደ በሽታው ዓይነት የሚለያይ ሲሆን ከ 5-7 የሚደርሱ ኩባያዎች በአንዴ የታማሚው ጀርባ እና የተለያዩ ክፍሎች ላይ ሊደረግ ይችላል፡፡
ይህ የህክምና ዓይነት አሁን አሁን የዘመናዊውን ህክምና ትኩረት እያገኘ እንደሆነ ያስነበበው webmed በዘርፉ የተካሄዱ ጥናቶች ግን ያን ያህል አይደሉም ብሏል፡፡
ሁለት (2) ዓይነት የዋግምት ዓይነቶች ያሉ ሲሆን እነርሱም ደረቅ እና እርጥብ የዋግምት ህክምና ዓይነቶች በመባል ይታወቃሉ፡፡
① ደረቅ የሚባለው የዋግምት ዓይነት የተቋጠሩ ጡንቻዎችን እና የጓጎሉ ደሞችን ለመፍታት ያለ ምንም የቆዳ መከፈት የሚከናወን ነው፡፡ ይኸውም ኩባያውን
ሰውነት አካል ላይ እያዘዋወሩ ለማሳጅነትም ያውሉታል፡፡
② እርጥብ የሚባለው ደግሞ በኩባያው የተሰበሰበውን የቆዳ ክፍል በትንሹ በመውጋት አልያም በመቅደድ እና የቆሸሸ ደም በማስወጣት የሚካሄድ
ሲሆን ይህኛው የዋግምት ዓይነት እጅግ ብዙ ለሆኑ በሽታዎች እንደሚጠቅም ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡
በዋግምት/ሂጃማ(cupping) አማካኝነት የሚወጣው ደም ምንድን ነው?
በዋግምት አማካኝነት የሚወጣው የተመረዘና(toxic) እና በጣም የጠቆረ ደም በህክምናው አጠራር congestion (tharembosis) statgmant blood ይባላል። ይህ ደም በደም መተላለፊያ ባንባዎች ላይ በመርጋት የደም ዝውውርን በማስተጓጎል(በማወክ) የተለያዩ በሽታዎችን ያመጣል። በሰውነት ላይም እባጭ (swollen) እጢ (tumor) እንዲፈጠርና ደም መላሽ ቧንቧዎችን በመዝጋት የልብ ህመምን (angina pectoris) እና ነጭ የደም ሴል ፣ ቀይ የደም ሴል ሄሞግሎቢን ላይ ችግር ይፈጥራል የቆዳና የከንፈር ቀለም እንዲቀየር ያደርጋል እንዲሁም ሰውነት ማሳከክ እና የመንደብደብ ባህሪ ያመጣል
የተበከለ ደም ከየት ይመጣል???
ይህ ዲኦክስጅኔትድ(deoxygenated) የሆነ ደም መምጫ መንስኤው የተበከለ አየር ወደ ውስጣችን ሲገባ ፣ የተዛባ አመጋገብ፣ብስጭት፣ንዴት፣በተደጋጋሚ የመውደቅ እና የመደብደብ አደጋ ካጋጠመዎት ሊከሰት ይችላል።
ሰለ ዋግምት ምንነት ይህን ያህል ካልንዎ ስለ ዋግምት አስገራሚ የጤና ጥቅሞች ደግሞ እነሆ ብለናል፡-
የዋግምት/ሂጃማ(cupping) ጥቅሞች
ለራስ ምታት ፡ጭንቀትእና ቅጥቅጣት
ለአስም እና ሳይነስ
ለወገብ ህመም, ለነርቭ, ለአላርጅክ, ለጡንቻ መሸማቀቅ, ለሪህ, ለብርድ, ቁርጥማት, ለድም ግፊት
ለሰውነት ክብደት እንዲሁም ለእጅና ለእግር ህመም።
ዋግምት ቆሻሻ ደምን ከማስወጣት ባለፈ የደም ትቦዎችን የማፅዳት እና ጤነኛ የደም ዝውውር እንዲኖር የማድረግ ኃይል ስላለው እንደ ብጉር፣ ችፌ ፣ ምርቅዝ እና የመሳሰሉ የቆዳ በሽታዎችን ለማከም እንደሚረዳ የዘርፉ ባለሙያዎችና በዘርፉ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች ጠቁመዋል፡፡
ሂጃማ የነቢዩ ሱና ነው!!
@ Dr Mohammed Beshir