sirajmuhammed shared a
Translation is not possible.

አላህ የነብዩላህ ሙሳን ህዝቦች ከፊርዐውን ነፃ ካደረገ ቡሀላ ወደ አሁኗ ፍልስጢን ሄደው እንዲኖሩ ነገራቸው።ሙሳም በአስራ ሁለት ነገዶች የተከፋፈሉትን ወደ ስድስት መቶ ሺህ የሚጠጉ ህዝቦቻቸውን ይዘው የከተማዋ መግቢያ ላይ ደረሱ።ያኔ አላህ ለሙሳ ገብተው ከነዋሪዎቿ ጋር እንዲዋጉ አዘዛቸው።

መጀመሪያ ሀገር ሰላም ብለው ሰተት ብለው ሊገቡ የመጡ ህዝቦችን''ተዋጉ'' በላቸው የተባሉት ነብይ ከየነገዱ ለህዝባቸው ተወካይ አድርገው የመረጧቸውን አስራ ሁለት ሰዎች ወደ ከተማዋ ገብተው ስለ ነዋሪዎቹ እንዲያጣሩ ላኩዋቸው።እዚህ ጋር ነበር ፈተናው...እነዛ ሰዎች ገብተው የነዋሪዎቹን አፈጣጠር ሲያዩ ረዣዥምና ግዙፎች ሆነው አገኟቸው።''እንዴት ከነዚህ ጋር ፍልሚያ ግጠሙ እንባላለን?''በሚል ስሜት ያዩትን ለሙሳ ዐለይሂ ሰላም ነገሯቸው።ሙሳም ነገሩን ከሰሙ ቡሀላ ወሬውን  ለማንም እንዳያደርሱ አስጠንቅቀው አላህ የሰጣቸው ቅዱስ መሬት ላይ ገብተው እንዲዋጉ ህዝቦቻቸውን እንዲህ በማለት መጣራት ጀመሩ....

يَا قَوْمِ ادْخُلُوا الْأَرْضَ الْمُقَدَّسَةَ الَّتِي كَتَبَ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَرْتَدُّوا عَلَى أَدْبَارِكُمْ فَتَنقَلِبُوا خَاسِرِينَ

«ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ፡፡ ወደ ኋላችሁም አትመለሱ፡፡ ከሳሪዎች ኾናችሁ ትመለሳላችሁና፡፡»

አትናገሩ የተባሉትን ሚስጥር ከሁለት ሰዎች በቀር የጠበቀ አልነበረምና ሁሉም ጋር የሰዎቹ ግዙፍነት መረጃ ደርሷል።ፊርዓውንን ያህል አመፀኛ ጌታ ነኝ ባይን ባህር ከፍሎ አሳልፏቸውና አስምጦላቸው ዛሬን እንዲያዩ ትልቅ ተዓምሩን ያሳያቸውን ጌታ እነዚህን ሰዎች ተዋጉ ብሎ ሲያዛቸው ሊያምኑትና እሺ ብለው ሊታዘዙት ሲገባ አሻፈረኝ በማለት የሰጡትን ምላሽ አላህ እንዲህ ይተርክልናል....

قَالُوا يَا مُوسَى إِنَّ فِيهَا قَوْمًا جَبَّارِينَ وَإِنَّا لَن نَّدْخُلَهَا حَتَّى يَخْرُجُوا مِنْهَا فَإِن يَخْرُجُوا مِنْهَا فَإِنَّا دَاخِلُونَ

«ሙሳ ሆይ! በርስዋ ውስጥ ኀያላን ሕዝቦች አሉ፡፡ ከርስዋም እስከሚወጡ ድረስ እኛ ፈጽሞ አንገባትም፡፡ ከርስዋም ቢወጡ እኛ ገቢዎች ነን» አሉ፡፡

ልክ ዛሬ ላይ የሙስሊም ሀገራት አላህን የሚያህል ታላቅ ጌታ እያላቸው እነ አሜሪካንን ሀያላን ናቸው ብለው በማሰብ ትንሽ መራመድ ተስኗቸው እጅ እግራቸውን አጣጥፈው እንደተመለከቱት ሆነ ነገሩ...

ሁሉም አንችላቸውም ብለው ተስፋ በቆረጡበት ሰአት አላህ የማሰብን ኒዕማ የሰጣቸው እሱ ድልን እንደሚሰጣቸው የተማመኑ ሁለት የሙሳ ዐለይሂ ሰላም ተወካዮቹ እንዲህ አሉ

قَالَ رَجُلَانِ مِنَ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِمَا ادْخُلُوا عَلَيْهِمُ الْبَابَ فَإِذَا دَخَلْتُمُوهُ فَإِنَّكُمْ غَالِبُونَ وَعَلَى اللَّهِ فَتَوَكَّلُوا إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

«ከእነዚያ (አላህን) ከሚፈሩትና አላህ በእነርሱ ላይ ከለገሰላቸው የኾኑ ሁለት ሰዎች «በእነርሱ (በኀያሎቹ) ላይ በሩን ግቡ፡፡ በገባችሁትም ጊዜ እናንተ አሸናፊዎች ናችሁ፡፡ ምእመናንም እንደኾናችሁ በአላህ ላይ ተመኩ» አሉ።

እዚህ ጋር የሀማስ ወታደሮችንና አጠቃላይ የፍልስጢን ህዝቦችን ወኔ አስታወሰኝ።አላህ ላይ በጣሙን እርግጠኞች ናቸው።ድልን እንደሚሰጣቸው አይጠራጠሩም።ግን አለም ላይ ካለው ሙስሊም አንፃር እንደዛኔው ሁለቱ ሰዎች ጥቂት ናቸውና''በጋራ ከተነሳን እናሸንፋለን በአላህ ላይ ተመኩ''ሲሉ ይጣራሉ።(የሚሰማ ባይኖርም)

የሙሳ ህዝቦች እነዚህን ሁለት ሰዎች ሊሰሟቸው ፍቃደኛ አልሆኑም።እንዲያውም ጭራሽ እንዲህ ብለው ቁርጣቸውን ነገሯቸው....

قَالُوا يَا مُوسَى إِنَّا لَن نَّدْخُلَهَا أَبَدًا مَّا دَامُوا فِيهَا فَاذْهَبْ أَنتَ وَرَبُّكَ فَقَاتِلَا إِنَّا هَاهُنَا قَاعِدُونَ

«ሙሳ ሆይ! በውስጧ እስካሉ ድረስ እኛ ፈጽሞ ምን ጊዜም አንገባትም፡፡ ስለዚህ ኺድ አንተና ጌታህ ተጋደሉ እኛ እዚህ ተቀማጮች ነን» አሉ፡፡

ይሄኔ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እነዚህን ህዝቦች ማነሳሳት እንደማይሆንላቸው ሲገባቸው የመጨረሻ አማራጫቸው የነበረው ወደ ጌታቸው መጣራት ብቻ ነበር።ከህዝባቸው ተስፋ ቆርጠው አላህን እንዲህ አሉት

قَالَ رَبِّ إِنِّي لَا أَمْلِكُ إِلَّا نَفْسِي وَأَخِي فَافْرُقْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ الْقَوْمِ الْفَاسِقِينَ

«ጌታዬ ሆይ እኔ ራሴንና ወንድሜን በቀር (ላስገድድ) አልችልም፡፡ በእኛና በአመጸኞቹም ሕዝቦች መካከል ለይ» አለ፡፡

በአላህ ላይ ቅንጣት ጥርጣሬ ሳይኖራቸው አብሯቸው የሚቆም አማኝ በማጣታቸው ምክኒያት ድልን የተነፈጉት ነብዩላህ ሙሳ በነሱ መሀከል አላህ እንዲለይ በምሬት እንደጠየቁት ዛሬም ነጋ ጠባ እንደ ቅጠል እየረገፉ አንድ እኛነታችን የሚፈቅድልንን ''ራሳችንን ከትላንታችን የመቀየር'' ትግል እንኳን የነፈግናቸው የፍልስጢን ወገኖቻችን''በመሀከላችን ለይ እንዳይሉብን''እሰጋለሁ።

አላህ የሙሳን ዐለይሂ ሰላምን ህዝቦችን ከተዋጉ ቅዱስ ምድርን ሊያጎናፅፋቸው ቃል የገባላቸው እሱ ላይ ያላቸውን እምነትና ታዛዥነታቸውን  ሊፈትሽ ነበርና ፈተናቸውን መውደቃቸውን ካረጋገጠ ቡሀላ እንዲህ ሲል ውሳኔውን አስተላለፈ

قَالَ فَإِنَّهَا مُحَرَّمَةٌ عَلَيْهِمْ أَرْبَعِينَ سَنَةً يَتِيهُونَ فِي الْأَرْضِ فَلَا تَأْسَ عَلَى الْقَوْمِ الْفَاسِقِينَ

እርስዋም (የተቀደሰችው መሬት) በእነርሱ ላይ አርባ ዓመት እርም ናት፡፡ በምድረ በዳ ይንከራተታሉ፡፡ «በአመጸኞችም ሕዝቦች ላይ አትዘን» አለው፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group