ማንኛውም ሙስሊም እነዚህን አራት ነገሮች ማወቅና መተግበር ግዴታው ነው። የመጀመሪያው እውቀት ነው እውቀት ሲባል:- አላህን ማወቅ፣ረሱልን ሰ.ዐ.ወ ማወቅና ኢስላምን ማወቆ ነው ።አላህን ማወቅ ሲባል ብቸኛ ተመላኪ መሆኑን ፣ፈጣሪ መሆኑን፣የሁሉ ነገር አስተናባሪ መሆኑን፣ፈራጅ ፣ሁሉ ነገር በእሱ እጅ እንዳለ ማመንና ይህንን ሁሉ ፍጥረተ ዐለም ፣መሊኢኮችን ያስገኘ በመሆኑ ፤አምልኮ ለእርሱ ብቻ እንደሚገባው አምኖ እርሱን ብቻ ማምለክ፣እርሱን ብቻ ፈራጅ ማድረግ ፣ለእስሱ ብቻ መዋረድ ይህንን ተግባራዊ ማድረግ ነው ።
መልእክተኛውም ዐ.ሰ የመጨረሻ መልእክተኛ መሆናቸውን ከእርሳቸው በኃላ መልእክተኛ እንደሌለ እንዲሁም ደግሞ በሁሉ ነገሮ ላይ የሳቸው ንግግር ተፈፃሚ መሆኑን የከለከሉት ክልከላን ደግሞ መከልከል እንዳለብን ማመንና ሌሎችም ሰፊ ተያያዥ ነጥቦች አሉ እነዚህን ማመን ግዴታ ነው ።
እንዲሁም እስልምናን ማወቅ ነው፣እስልምና መሰረቶች አሉት ፣አርካኖች አሉት እነዚህን ሁሉ ጠብቆ መተግበር ግዴታ ነው።
ይህን ሁላ ደግሞ ከመረጃ ጋር ማወቅ፣በህይወት ዘመን አንዴ እንኳ ቢሆን ማወቅ የግድ ነው።
ሁለተኛው ደግሞ ባወቅነው ነገር ተግባራዊ ማድረግ ነው። ሰዎች የተለያዩ ናቸው አንዳንዱ ያለ እውቀት የሚሳሳት አለ ፣በስሜት ብቻ መልካምን ነገር እተገብራለው ብሎ በማሰብ ብቻ በቀናነት የሚሳሳት አለ ፣ ያለ እውቀት ባለማወቁ የተነሳ፣
ሌሎች ደግሞ እውቀት ኖሯቸው ከእውቀት ጋር የሚጠሙ አሉ !
እነዚህን ሁለት ባህሪ የተላበሱ ሰዎችን አላሁ ሱዐ በቁርኣን ላይ አስጠንቅቆናል ።
غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ
እነዚህ አንደኞቹ የተረገሙና አላህ የተቆጣባቸው ናቸው ሁለተኞቹ ።
እነዚህም ነሳራና የሁዶች ናቸው ማለት ነው ። አንደኞቹ ነሳሮች መልካምን ነገር መስራት ፈልገው ነገር ገን ያለ እውቀት ስለሰሩ ተሳሳቱ ፤የሁዶች ደግሞ እያወቁ ባወቁት ነገር አልሰሩምና ወደጥፋት አመሩ ማለት ነው ። እነዚህን ሁለት መንገዶች እንዳንተገብረው አላህ አስጠነቀቀን ማለት ነው ።
ያዘዘን ፣እንድንተገብረው የሚፈልገው ቀጥተኛ መንገድ እነዛ ነብያቶችን፣ሹሃዳዎችን፣ሷሊሖችን እንዲሁም ደግሞ ሲዲቆችን ፣እውነተኛ ሰዎችን የመራበትን የሆነውን ቀጥተኛውን መንገድን ምራን ብለን እንድንለምነው ያዘዘንን መንገድን ነው ማለት ነው ።
ስለዚህ ማወቅ አንዳለ ሆኖ ባወቅነው ነገር መተግበርም ግዴታ ነው ማለት ነው።
ይህም ብቻ አይደለም ካወቅን በኃላ ደግሞ ለሌሎች ዳዕዋ ማድረግ የግድ ነው፣ይህንን ያወቅነውን ነገር ሌሎች እንዲተገብሩት ማስተማር የግድ ነው ።
ከዛ ደግሞ ይህንን ያወቅነው ነገር ስናስተምር
ሰዎች የመቀበል ደረጃቸው ይለያያል ፣ወዶ የሚቀበል አለ ፣አሻፈረኝ የሚል አለ፣አሻፈረኝ ብሎም ጉዳት ሊያደርስ የሚፈልግ አለና እነዚህን ነገራቶች በአጠቃላይ ዳዕዋ ስናደርግ፣ሰዎችን ወደ መልካም ጎዳና ስንጠራ በሚደርስብን አዛ (ችግር) ሰብር እንድናደርግ ያዘናል ማለት ነው።
ስለዚህም አራት ነገራቶችን ሁሉም ሰው ሊያሟላ ይገባል
የመጀመሪያው ማወቅ ነው ፣ከዛም መተግበር፣ከዚያ ደግሞ ያወቅነውን የተገበርነውን ለሰዎች ማድረስ ፣መጣራት፣ከዛ ደግሞ ከሰዎች የሚመጣውን መጥፎውን አደጋ ትዕግስት አድርጎ ማለፍ ነው።
ይህንን አሊህ በቁርአን ላይ በአንድ ሱራ ሊይ ያሰፍረዋል
وَالْعَصْرِ
إِنَّ الْإِنسَانَ لَفِي خُسْرٍ
በጊዜ እምላለው ብሎ አላሆ ሰዎች ሁሉ ኪሳሪ ውስጥ ናቸው አለ።
إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَتَوَاصَوْا بِالْحَقِّ وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ
አላህ እነዚያ ያመኑ፣ባወቁት ነገር የተገበሩ ፣መልካምን የሰሩ ፣በእውነት አደራ የተባባሉ ፣በትዕግስት ላይ አደራ የተባባሉ ሲቀሩ ፤እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸውን አራት መስፈርቶች ያሟሉ ሲቀሩ ሁሉም ኪሳራ ውስጥ ነው ይላል ።
ይህንን አስመልክቶ ኢማሙ ሻፊዒይ ረሒመሁላህ አላህ ከዚህ ቁርአን ውጪ ሌላ የቁርአን ሱራን ባያወርድ ኖሮ ለሰዎች ከመረጃ አንፃር በቂ ነበር ብለዋል ማለት ነው።
ወሰላሙ ዐለይኩም