Translation is not possible.

👉 የኢኽዋንና ሙመዪዓ ጥምር መጅሊስ ለሚያደናብራቸው

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ በፌዴራል ደረጃ እውቅና ተሰጥቷቸው የተደራጁና ፈቃድ የተሰጣቸው የሱና ተቋማት በኢኽዋንና ሙመዪዓ ጥምሩ መጅሊስ እንግልት እየደረሰባቸው ነው ። በጣም የሚገርመው እነዚህ የሱና መድረሳና መስጂዶች የአሕባሹ መጅሊስ በነበረበት ጊዜ በሰላም ያለ ምንም ጥያቄ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ መሆኑ ነው ። ምናልባት ያጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝቦች የሚመሩበት ህገመንግስት ለዜጎች የሰጠው የእምነት ነፃነትና የመማር የማስተማር እንዲሁም የመደራጀት መብት የበለጠ ገብቷቸው ሊሆን ይችላል ።

ያውም የአሁኑ መጅሊስ በአዋጅ ሲቋቋም ይህን የዜጎች መብት መንካት እንደማይችል በመመሪያው ላይ በግልፅ ተቀምጦ ሳለ ነው የህገመንግስቱንም የአዋጁንም መመሪያ በመጣስ የዜጎችን መብት እየነፈጉ ያሉት ።

ከላይ እንደምታዩት አዋጁ ሲፀድቅ ከዚህ በፊት በፌዴራልም ይሁን በክልል የተቋቋሙ የሙስሊሞች የእምነት ተቋማትም ይሁን ወደ ፊት የሚደራጁትን መብት መከልከል እንደማይችል በግልፅ ተቀምጧል ። ይሁን እንጂ እነዚህ አካላት ከተወሰኑ በጥቅም ከያዙዋቸው የህግ አካላት ጋር በመሆን የዜጎችን መብት እየገፈፉና እንዲታሰሩ እንዲገላቱ እያደረጉ ነው ።

በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያላችሁ ሰለፍዮች መብታችሁን አውቃችሁ እነዚህን አካላት ወደ ፍርድ ቤት በማቅረብ በእስር ላይ ያሉ ወንድሞቻችሁን ማስፈታትና መብታችሁን ማስከበር ትችላላችሁ ። አላህ ከግፈኞች ተንኮል ይጠብቋችሁ ።

https://t.me/bahruteka

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group