Translation is not possible.

🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿

ኢትዬጲያ ውስጥ ሆናችሁ ስለፍልስጤም እና እስራኤል ምን ያገባቹሃል ለሚለው ወቀሳ እየሩሳሌም ለሙስሊሞች ሶስተኛ  ቅዱስ ስፍራ በመሆኗ በውስጧ ያለውን መስጂደል አቅሳ ከእምነታችን ጋር ትልቅ ቁርኝት ያለው በመሆኑ የእየሩሳሌም ጉዳይ የፍልስጤማውያን ብቻ ሳይሆን የመላው  አለም ሙስሊም ጉዳይ በመሆኑ  በቀጥታ ስለሚመለከተን መሆኑን  ሁሉም ሊረዳልን  ይገባል፡፡ በኢስላም ቅድስት ከተማ ለሆኑት ለመካ እና ለመዲና ሙስሊሞች እንደሚቆረቆሩ ሁሉ ሶስተኛ ቅዱስ ለሆነችው ለእየሩሳሌም ለመስጂደል አቅሷም ሁሉም ሙስሊም እንደሚቆረቆር ሊታወቅ ይገባል፡፡ የእየሩሳሌም የመስጂደል አቅሷ  በፂዬናውያን ወረራ ስር ሆኖ ጥቃት ሲደርስበት   የሚያመን፣የሚያስቆጣን እና የሚያስቆጨን ስፍራው በኢስላም  የተቀደሰ በመሆኑ ከሃይማኖታችን ጋር ትልቅ ቁርኝት ያለው በመሆኑና የወንድሞቻችን በግፍ መገደልና መሰቃየት የኛም ህመም መሆኑን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል፡፡

ኢብኑ ተይሚያህ(ረሂመሁላህ)እንዲህ ይላሉ

"ሙእሚን ሙእሚኖችን በሚያስደስት ነገር ይደሰታል፣እነሱን ያስከፋ ነገርም ያስከፋዋል። እንደዚ ያልሆነም ሰው ከእነርሱ አይደለም።"

📚(መጅሙዕ አልፈታዋ 2/373)

መስጂድ አል-አቅሷ  የቦታና የመስጂድ ሥም ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ሃይማኖት ጋር የሚያገናኙት በርካታ ቁምነገሮች አሉ ከነሱ ውስጥ በጥቂቱ ፦

🕌አቅሷ ማለት፦

አምላካችን አላህ (ሱ.ወ.) መስጂድ አል-አቅሷን እና  ዙሪያውን በሱ የተባረከና የተቀደሰ አካበቢ መሆኑን በቁርአን ላይ ገልፆልናል፡፡

🕌አቅሷ ማለት፦

  

ነብዩﷺ ከጌታቸው ሰላት ለመቀበል ወደ ሰማይ ሲወጡ ጉዞ ያደረጉባት መስጂድ ናት።

    [አል_ኢስራእ:1]

🕌አቅሷ ማለት፦

  ሙስሊሞች ከሂጅራ በኋላ ለአስራ ሰባት ወራት አካባቢ ተቀጣጭተው የሰገዱባት የመጀመሪያዋ ቂብላ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

  መካ ከምትገኘው መስጂደል ሓራም እና መዲና ከምትገኘው መስጂደል ነበዊ ቀጥሎ ጓዝ ጠቅልሎ መሄድ የተደነገገላት ሶስተኛዋ መስጂድ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

ነብዩﷺ ኢስራእ ባረጉበት ሌሊት  ሁሉም ነብያቶች ተሰብስበውላቸው ኢማም ሆነው ያሰገዱባት መስጂድ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

መስጂደል ሓራም እና መስጂደል ነበዊ ሲቀር ሌላ ቦታ ከሚሰገድ ሰላት እሷ ላይ ሲሰገድ አምስት መቶ እጥፍ በላጭነት ያለው መስጂድ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

   ከመስጂደል ሓራም ቀጥሎ ምድር ላይ የተገነባችው ሁለተኛዋ መስጂድ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

   አላህ እሷንም ዙሪያዋንም በረካ ያደረጋት የሆነች መስጂድ ናት። {…الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ…}

🕌አቅሳ ማለት፦

    ነብዩላህ ሙሳﷺ አላህ ወደ እሷ አስጠግቶ እንዲያሞተው እና እዝያው አካባቢ እንዲቀበር የተማፀነው ቦታ ናት።

🕌አቅሷ ማለት፦

 

ቡኻሪ በዘገበው ነብዩﷺ እንዲህ ይላሉ፦

«ነብዩ ሱለይማን መስጂደል አቅሷ ገንብቶ ካጠናቀቀ በኋላ ለአላህ ሶስት ነገር እንዲሰጠው ለመነው። "ፍርዱ የአላህን ፍርድ እንዲገጥም፣ ለማንም ሰው የማይሰጥ የሆነ ንግስና እንዲሰጠው እና ማንኛውም ሰው ሰላትን ለመስገድ ብቻ ፈልጎ ወደዚህ መስጂድ የመጣ እንደሆነ ከመስጂዱ ሲወጣ እናቱ እንደ ወለደችው ቀን ከወንጀሉ የነፃ ሆኖ እንዲወጣ" ነብዩﷺ ሁለቱ እንኳ በእርግጥም ተሰጥቶታል፤ ሶስተኛውም እንደ ተሰጠው እከጅላለሁ» ብለዋል።

🕌አቅሷ ማለት፦

  የቂያማ ቀን መቀስቀሻዋ ምድር ናት። መይሙና ቢንት ሳዕድ አስተላልፋው ኢማሙ አልባኒ ሰኺኽ ብለውታል።

🕌አቅሷ ማለት፦

ለመጀመሪያ ጊዜ የገነባው ከፊሎች አባታችን ኣደም፣ ከፊሎቹ የነብዩ ኑሕ ልጅ፣ ሌሎቹ ደግሞ ነብዩ ኢብራሂም እንደ ገነቧት ይዘግባሉ። ከዝያም ነብዩላህ ሱለይማን አሳምረው እንደገነቧት ታሪክ ዘጋቢዎች ያወሳሉ።

 

🔻አልአቅሷን ከጎበኙ ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ፣ አቡ ዑበይዳ፣ የምእመናን እናት ሶፍያ ፣ ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል፣ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር፣ ኻሊድ ኢብኑ አልወሊድ፣ አቡ ዘር፣ አቡ ደርዳእ፣ ሰልማን አልፋሪሲይ፣ ዐምር ኢብኑ አልዓስ፣ ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ፣ አቢ ሁረይራ፣ ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

🔻በርካታ ትላልቅ የሙስሊሙ ዓለም ሊቃውንትም ለትምህርትና ለኑሮ ወደዚያው ተጉዘዋል፡፡ ታዋቂው ሙፈሲር ሙቃቲል ቢን ሱለይማን፣ ኢማም አልአውዛዒ፣ ኢማም ሱፍያን አስሠውሪይ፣ ኢማም ለይሥ ኢብኑ ሰዕድ፣ ሻፊዒይና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

መስጂደል አቅሳን ከተረገሙት ፂዬናውያን እጅ አላህ ነፃ ያውጣልን!!ከመሞታችንም በፊት ወደ እየሩሳሌም ተጉዘን በመስጂደል አቅሳ ለመስገድ ሁላችንንም አላህ ያብቃን!!

ያ ረብ! የፈለስጢን ወንድሞቻችን ስቃይ የሚያበቃበትን ግዜ ቅርብ አድርገው!!!

🤲اللهم نستودعك ‌ فلسطين وأهلها ، أمنها وأمانها ليلها ونهارها أرضها وسماءها رجالها ونساءها شيوخها وأطفالها وشبابها..

اللهم فاحفظهم من كل شر اللهم ثبت أقدامهم وسدد رميهم وامددهم بجنود من عندك يا ناصر المستضعفين

اللهم عليك بأعدائهم اللهم اقتلهم بددًا ولا تبقى منهم أحد

اللهم زلزل الأرض من تحت أقدامهم

وشتت شملهم وفرق جمعهم وشل أوصالهم

وأرنا فيهم يومًا أسودًا يشفي صدور قوم مؤمنين 🤲🏼

copy

https://t.me/hamzaibnudinoislamicmedia

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group