Translation is not possible.

" ሀማስ ህዝቡንና ሀገሩን ነፃ ለማውጣት የሚታገል የነፃነት ታጋይ  ቡድን ነው "

             ፕሬዚዳንት ረጄብ ጦይብ ኤርዶጋን !

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ሀማስ የነፃነት ታጋይ እንጅ  አሸባሪ ቡድን አይደለም ሲሉ ተናገሩ ።ፕሬዝዳት ኤርዶጋን ይህን ያሉት የምእራባውያን ሀገራት መንግስታት ሀማስን በአሸባሪነት እየፈረጁ መሆናቸውን ተከትሎ ነው ።

በተለይም ኢስላም ጠሉ ነፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ማኑኤል ማክሮን ትላንት እስራኤልን ሲጎበኝ ከቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በሰጠው መግለጫ " ሀማስ ልክ እንደ አይኤስ አይኤስ አሸባሪ ድርጅት በመሆኑ አለምአቀፍ ጦር ተመስርቶ ሀማስን መደምሰስ አለበት " ማለቱ ኤርዶጋንን ማስቆጣቱ አልቀረም ። እስራኤል ብቻዋን ሀማስን ማጥፋት እንደማትችል የተረዳው ማክሮን አለምአቀፍ ጦር አቋቁመን ሀማስን እንዋጋ ማለቱ በርግጥ የፕሬዝዳንቱን እጅግ ባለጌነትና ጋጠወጥነት ያሳየ ፈረንሳይ ዛሬም የሙስሊሙ አለም ጠላትነቷ የገነገነ መሆኑን ማሳያ ነው ።

ለዚህ መልስ ይመስላል ኤርዶጋን ሀማስን " ወረራና ግፍን ለመቀልበስ መሬቱንና ህዝቡን ነፃ ለማውጣት የሚታገል የነፃነት ታጋይ እንጅ እናንተ እንደምትሉት አሸባሪ አይደለም " ሲሉ መግለጫ የሰጡት ።

እስራኤል ጦሯን በእግር አዘምታለሁ ብላ ደርድራ ግና ወደ ጋዛ መግባት በሞት መንጋጋ ውስጥ መግባት መሆኑን በማወቋ እስካሁን ባለችበት ረግጣለች ።

ሀማስን ማጥፋት ቀርቶ ማዳከም ያቃታት እስራኤል ምእራባውያንን እርዱኝ በማለት ጭምር ዘመቻ ስትከፍት የኖረች ቢሆንም ያ እንደማይሳካላት አውቃዋለች ። ንፁሀንን በአየር ከመጨፍጨፍ ያለፈ ድልም ማግኘት አልቻለችም ።

ታድያ በዚህ የሀማስ አለመሸነፍ የተበሳጨው ማክሮን " ለምን አንድ የጦር ግንባር ፈጥረን ሀማስን አንዋጋም " ሲል ለምእራባዊያን ጥሪውን አስተላልፏል !

#seid_mohammed_alhabeshiy

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group