Translation is not possible.

ምዕራቡ አለም በብሪቴይን እርግዝና በፈረንሳይ አዋላጅነት በጥቅመኛ አረቦች አጨብጫቢነት የወለዷትን የግፍና የበደል ልጅ መጠበቅ ላይ መተባበር መያዛቸው ብዙ አያስገርምም። ታማኝነት አልባ፣ የሁለት ሚዛን ባለቤት ከሆኑት የግፍ መሪዎችና ልሂቃን ስብስብ ከዚህ የተለየ መጠበቅም የዋህነት ነው። ቅሉ ሁሉም ነገር ማብቂያ አለው፤ ሁሉም ነገር መጠናቀቂያ አለው።

★ ማብቂያውም ፍትህን ለተነፈጉት ሁሉ ብርሃን መሆኑ ነው። ወላዱም፣ ያዋለደውም፣ ያጨበጨበውም፣ የተወለደውም የበደልና የግፍ ልጅም መዋረዳቸው አይቀርም። በነፍሶቻቸው ውስጥ የነገቡት የበላይነትና ሁሉን አድራጊነት መንፈስ ቅዠት መሆኑ አይቀርም። የአላህ ቃል እንዲህ ይላል።

« إن الذين كفروا ينفقون أموالهم ليصدوا عن سبيل الله فسينفقونها ثم تكون عليهم حسرة ثم يغلبون… »

« እነዚያ የካዱት ሰዎች ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘባቸውን ያወጣሉ። በእርግጥም ያወጣሉ። (ካወጡም በኃላ) ፀፀት ትሆንባቸዋለች። ከዚያም ይሸነፋሉ። የካዱት ሰዎች ወደ ገሀነምም ይሰበሰባሉ።»

እንዲህም ይላል።

« …عسى الله أن يكف بأس الذين كفروا والله أشد بأسا وأشد تنكيلا »

« … አላህ የካዱትን ሰዎች ኃይል ሊከለክልልህ ይከጀላል (ይከለክልልሃል)። አላህም በኃይል ሲይዝ የበረታ፤ ቅጣቱም እጅግ ጠንካራ ነው። »

★ በተቃራኒው በበደል ውስጥ በትግልና በትእግስት፣ በትእግስትና በትግል ያለፉት ሁሉ የአላህ እርዳታ እየጨመረላቸው፤ እዝነቱንና እገዛውን እያሰፋላቸው፤ የድልን ካባ እንደሚያጎናፅፋቸው እርግጥ ነው።

ለተወዳጁ መልእክተኛው (ሰዐወ) አላህ እንዲህ ይላቸዋል።

« …فسيكفيكهم الله وهو السميع العليم »

« … ከእነርሱም (ከከሃዲያኑ) አላህ ይበቃሃል። እርሱ ሰሚና ዐዋቂው ነው። »

እንዲህም ይላል።

« أليس الله بكاف عبده ويخوفونك بالذين من دونه… »

« አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን? ከእርሱ ውጪ (በታች በሆኑት ጣኦቶቻቸው) በሆኑት ነገሮች ያስፈራሩሃል። … »

اللهم افرغ على المجاهدين الصابرين الصبر وانصرهم على الظالمين الغاصبين

#الأقصى حياتنا

والموت في سبيلها اسمى امانينا

Send as a message
Share on my page
Share in the group