Translation is not possible.

ጂሃድ

~

ጂሃድ የሙእሚኖችን ወኔ የቀሰቀሰ፣ የሙሽ - ሪኮችን እብሪት ያስተነፈሰ፣ የነ ፋርስና የነ ሮማን የትእቢት ማማ ያፈረሰ የእምነታችን መከበሪያ፣ የኢስላም ጉልላት ነው። ጂሃድ የመስዋዕትነት ጫፍ የዒባዳዎች ቁንጮ ነው።

ግና

★ ጂሃድ ማለት መስቀለኞች በፍልስጤም ምድር እንዳደረጉት ህፃናት፣ አዛውንት፣ ሴቶች እና ቀሳውስት ሳይለዩ በጅምላ መጨፍጨፍ አይደለም።

★ ጂሃድ ማለት እነ አፄ ዮሐንስ እንዳደረጉት አእላፍ ሰላማዊ ህዝብ አጋድመህ የምታርድበት የጅምላ ፍጅት አይደለም።

★ ጂሃድ ማለት የምኒልክ ጦር እንዳደረገው የሌሎችን እምነት ቦታዎች እያፈረሱ በቤተ ክርስቲያን መተካት አይደለም።

★ ጂሃድ ማለት ዛሬ ደም የጠማቸው አፍለኞች እንደሚያደርጉት በየመስጂዱ፣ በየ ቤተ ክርስቲያናቱ፣ በየትራንስፖርቱ፣ በየሆቴሉ ሰላማዊ ሰዎችን ማሸበር አይደለም።

★ ጂሃድ ማለት በቀን አስራ ሁለት ጊዜ ሙዱ የሚቀያየር የመንደር ወፈ.ፌ በአፀፋ መልክ የሚያውጀው የሰፈር ጥል አይደለም።

ባጭሩ ጂሃድ ልክ እንደ ሶላት፣ እንደ ፆም፣ እንደ ሶደቃ፣ እንደ የትኛው ዒባዳ የእምነታችን ክፍል ነው። እንኮራበታለን እንጂ አናፍርበትም።

በውር .ጋጥ አሸባሪዎች የተነሳ ይሄ የእምነታችን ክፍል ትልቅ ማጠልሸት ተፈፅሞበታል።

ዛሬ:

* ጂሃድ ማለት ሰላማዊ ህዝብ በተሰበሰበበት አጥፍቶ መጥፋት የሚመስላቸው ስንቶች ናቸው?

* ጂሃድ ማለት ዲፕሎማቶችን መግ.ደል፣ ማቃጠል፣ አስከሬን መጎተት የሚመስላቸው ስንቶች ናቸው?!

* ጂሃድ በከባዱ ከመጠልሸቱ የተነሳ ገና ርእሱ ሲነሳ ላብ የሚያጠምቃቸው ሙስሊሞች ስንት ናቸው?

* ዛሬ ጂሃድንና የኢስላምን ውበት እያጠለሸ ያለውን የሽብር ድርጊትን የማይለዩ ካ*ፊ*ሮች ቀርቶ ሙስሊሞቹ እራሱ ስንትና ስንት ናቸው?

* ጂሃድን እደግፋለሁ ማለት ሽብር እደግፋለሁ ማለት የሚመስላቸው ስንቶች ናቸው?

* ጂሃድ እንደ ሶላት፣ እንደ ዘካ፣ የእምነቴ ክፍል ነው ማለትን "ሰላማዊ ዜጎችን የማሸበር የሌት ከቀን ህልም አለኝ" ማለት አድርገው የሚረዱ ስንት ናቸው?

ለዚህ ሁሉ የተዛባ ግንዛቤ በእቅድ ከሚያጠለሹት በላይ ቀዳሚ ተጠያቂዎቹ እኛው ነን። ትክክለኛውን የጂሃድ ፅንሰ ሃሳብ ለሌሎች ከማድረሳችን በፊት እራሳችን ልንረዳ ይገባል።

√ በጂሃድ ጦረኛ ያልሆኑ ሰላማዊ ሰዎች ኢላማ አይደረጉም።

√ በጂሃድ ህፃናት ፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች እና ቀሳውስት ኢላማ አይደረጉም።

√ በጂሃድ የእምነት ቦታዎች ኢላማ አይደረጉም።

√ በጂሃድ ሌላው ቀርቶ ፍሬ ያፈሩ ዛፎች እንኳን አይቆረጡም።

√ በአሁኑ ሰአት በአንዳንድ ቡድኖች በኢስላም ስም እየተፈፀመ ያለው የሽብር ተግባር በፍፁም ጂሃድ አይደለም። የዑለማእ ድጋፍም የለውም።

√ ጂሃድ በሙስሊሞች መሪ ጥሪ እንጂ ጭምብል በለበሱ ጎረምሶች የሚታወጅ አይደለም።

ዛሬ ሃገራት የራሳቸው የመከላከያ ሚኒስቴር አላቸው። ሲያሽሞነሙኑት እንጂ ይሄ መከላከያ ሳይሆን የጦር ሚኒስቴር ነው። ይህ የጦር ሚኒስቴር ሃገርንና ዜጎችን ከጥቃትና ከስጋት ይጠብቃል። አስፈላጊ ሲሆን የሌላ ሉአላዊት ሃገር ድንበር ጥሶ ወረራ ወይም ጥቃት ይፈፅማል። ይሄ ዛሬም "በሰለጠነው" አለም በሰፊው የሚታይ እውነታ ነው። ሶማሊያ ላይ የስንት ሃገራት ጦር እንደተሰበሰበ ተመልከት።

ጂሃድ ሲባል የተለየ ምልከታ አይኑርህ። ልክ እንዲሁ እምነትን፣ ሃገርን፣ ድንበርን፣ ዜጋን፣ ለማስከበር የሚታወጅ ዘመቻ ነው። እናም የሙስሊሞች መሪ አስፈላጊ እንደሆነ ሲያምንበት ጂሃድ ያውጃል። ስለዚህ በየትኛውም እምነት በየትኛውም ሃገር ስም ጦርነት ሲካሄድ እንዳልኖረ የኢስላምን ጂሃድ በተለየ አይን መመልከትና ማጠልሸት ከሚዛናዊነት በእጅጉ መራቅ ነው።

=

( Ibnu Munewor ፣ መጋቢት 29/2011)

የቴሌግራም ቻናል፦

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group