Abu Ayub shared a
Translation is not possible.

🚫:::::::::ሰኸረተል መዉት:::::::::🚫

አንድ ሰዉ ለ#ሶስት /3 ቀናት በሰኸረተል መዉት ተሰቃየ ባለቤቱ ረሱል ( ﷺ ) ዘንድ አቀናች፡፡

ወይ ሞቶ አያሳርፈን እሱም አያርፍ ወይ ምላሱ ሸሐዳ አትል ግራ ገባን እኮ ያ ረሱለላህ ( ﷺ ) አለቻቸዉ፡፡

ረሱል ( ﷺ ) እናቱን አምጡልኝ አሉ፡፡ እናቱም ተጠርታ መጣች፡፡ ልጅሽ ምን አይነት ሰዉ ነዉ? ብለዉ ጠየቋት፡፡ እናትየዉም እንዲህ በማለት መለሱላቸዉ:– ከሰጋጆቹ ከዛኪሮቹ መሀል ነዉ አለቻቸዉ፡፡

ረሱልም ( ﷺ ) እሱን አደለም የምልሽ ካንቺ ጋራ እንዴት ነዉ? አሏት፡፡ እሷም ልቤ አዝኖበታል ያ! ረሱለላህ ( ﷺ ) ዋሽቼዎት በዋሕይ መጋለጥን አልፈልግም፡፡ ፈገግተኛ ፊቱን ለሚስቱ ኮስታራዉን ለኔ፣ መልካም ንግግርን ለእሷ ለዛ ቢሱን ለኔ፣ ከምግብ ጥሩዉን ከልብስ ቆንጆዉን ለእሷ እሷ ከመረጠችዉ የተረፈዉን ለኔ ስትል ብሶቷን ገለፀች፡፡

ይህኔ ረሱልም ( ﷺ ) እሳት አምጡልኛና ላቃጥለዉ አሉ፡፡ እናቲቱ ጮኸች ያ! ረሱለላህ ( ﷺ ) ልጄ የአካሌ ክፋይ እኮ ነዉ፡፡ ነብሴን ፊዳ አደርግለታለሁ አትንኩት አለች፡፡

ረሱልም ( ﷺ ) ይህን እኮ ነዉ የምልሽ አንቺ ይቅርታሽን ካልሰጠሽዉ የጀነትን ሽታ አያገኝም አሏት፡፡ ይኸዉ ጌታዬ መልዕክቶቹም ከልቤ ይቅር እንዳልኩት ምስክሮቼ ናቸዉ አለች፡፡ ሰዎችን ወደ ሰዉዬዉ ቤት ላኩ፡፡ ሰዉየዉም ሸሐዳ ከምላሱ እንደወጣ ነብስያዉ ወጣች።

✍ወዳጄ ሆይ!

ባልዋን በጀነት ማግኘት የምትፈልግ ሴት በእናቱ ሐቅ ላይ ታበረታዋለች ጀነትን የሚመኝ ሰዉ በወላጆቹ ሐቅ አይደራደርም፡፡ ከአላህ ሐቅ ቀጥሎ ከባዱ የነሱ መሆኑን አይዘነጋም እነሱ ማለት አጥፍተህም የሚወዱህ ዉብ ልቦች ናቸዉና ሁሌም ብታጠፋ ሁሌም ሁሌም ይቅርታን ጠይቅ። አደራ አደራ.።#ሼር በማድረግ ያስተላልፉ

Send as a message
Share on my page
Share in the group