Translation is not possible.

#የስኳር_በሽታ

• የስኳር በሽታ ማለት ሰውነታችን ግሉኰስ (ስኳር) የሚባለውን ንጥረነገር መጠቀም ባለመቻሉ የሚፈጠር ችግር ነው። በዚህ ጊዜ በደም ውስጥ ያለው የግሉኰስ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።

• ይህ የሚሆነው ደግሞ በሶስት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው።

1. ቆሽት ውስጥ የሚገኝ ህዋስ (ሴል) ኢንሱሊን የሚባለውን ሆርሞን ማምረት ባለመቻሉ የኢንሱሊን መጠን በመቀነሱ

2. ሰውነታችን ወይም ህዋሳት ኢንሱሊንን ተላምዶ ኢንሱሊኑ ጥቅም የማይሰጥ መሆኑ።

3. ቆሽት ውስጥ ኢንሱሊንን የሚያመርተው ቤታ ሴል በተለያየ ምክናየት በመጎዳቱ ነው።

#በዚህ የተነሳ

1. ሰውነታችን ስኳርን በበቂ ሁኔታ አይጠቀምም።

2. የስኳር ምርትና መጠን በደም ውስጥ ይጨምራል።

3. ኢንሱሊን ችግሩን መቆጣጠር አይችልም።

#ኢንሱሊን ማለት ቆሽት ውስጥ የሚመረት ሆርሞን ሲሆን በደም ውስክ ያለው የስኳር መጠን እንዳይጨምር የሚያደርግ ነው።

#ኢንሱሊን የስኳር መጠን በደም ውስጥ እንዳይበዛ የሚያደርገው በሶስት መንገዶች ነው።

1. ደም ውስጥ የነበረውን ስኳር ወደ ጉበት ወስዶ እንድጠራቀም በማድረግ

2. በደም ውስጥ የነበረውን ስኳር ጡንቻ ውስጥ እንድጠራቀም ማድረግ

3. በደም ውስጥ የነበረውን ስኳር እያንዳንዱ ሴል በአግባቡ እንድጠቀመው በማድረግ ነው።

#በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ጨመረ የሚባለው በስኳር መጠን መለኪያ መሳሪያ (Gluco Meter) ተለክቶ ሲሆን ይህም

1. ለ8 ሰአት ያህል ሳይመገብ ይለካና ከ126 mg/dl በላይ ከሆነ

2. ምግብ በልቶ ሲለካ ከ200 mg/dl በላይ ከሆነና ሌሎችም ማረጋገጫዎች አሉ።

በምርመራ ወቅት የሚደረግ ጥንቃቄ

1. የደም የስኳር መጠን ምርመራ ውጤት ከቁርስ በፊት ወይስ በኋላ መሆኑን ማረጋገጥ ።

2. ከቁርስ/ምግብ በኋላ የተወሰደ ናሙና ስኳር የሚያመለክት ከሆነ እንደገና ከቁርስ በፊት ናሙና በመወሰድ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

3. የስኳር መጠን ከፍ ማለቱ ወጥነት ያለው መሆን አለበት/persistent hyperglycemia.

ህፃናት ላይ ከሆነ የስኳር ህመም የእድሜ ልክ ህመም ነው ፤ የደም የስኳር መጠን ለረጅም ጊዜ ከልክ በላይ መጨመር ነው። እስካሁን ድረስ መተኪያ መድሀኒት እንጅ ፈውስ የለውም። የስኳር ህመምን መከላከል እና መቀነስ ይቻላል።

.

የደም የስኳር መጠንን የሚቆጣጠሩ በቆሽት የሚመረቱ ሁለት ተቃራኒ ቅመሞች አሉ እነሱም ኢንሱሊን እና ግሉካጎን ይባላሉ።

.

#ኢንሱሊን - Insulin

- ከምግብ በኋላ የደም የስኳር መጠን ሲጨምር ከቆሽት ወደ ደም ስር በመለቀቅ ለጊዜው አገልግሎት ላይ የማይውለውን የስኳር መጠን ወደ ጡንቻወቻችን፣ ወደስብ እና ወደ ጉበት ውስጥ እንዲሰርግ በማድረግ የስኳር መጠንን ያስተካክላል።

.

#ግሉካጎን - Glucagon

- የሰውነት የስኳር መጠን ሲያንስ በጡንቻ፣ በጉበት እና በስብ መልክ ከተከማቸው ግላይኮጅን ግሉኮስ እንዲመረት በማድረግ የደም የስኳር መጠን ከፍ እንዲል ያደርጋል።

#የስኳር_ህመም_ስርጭት

• በዓለም ላይ የስኳር ህመም በየአመቱ በእጅጉ እየጨመረ መሆኑን አሀዞች ያሳያሉ (በተለይ አይነት ሁለት ስኳር )።

• የህመሙ ስርጭት በዓለም ከቦታ ቦታ ይለያያል። ከጥቁሮች ይልቅ ነጮች ላይ ይበዛል።

ስኳር በየትኛውም እድሜ ክልል ሊከሰት ይችላል።

- የአይነት አንድ ስኳር ህመም በየትኛውም የህጻናት

እድሜ ሊከሰት ቢችልም ከ4-6 አመት እና ከ10-14 አመት ባለው እድሜ ክልል የመከሰት እድሉ ይጨምራል።

-ስኳር በዘር የመተላልፍ እድል አለው። ከአይነት አንድ ይልቅ አይነት ሁለት ስኳር በዘር የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው።

-በዘር ግንድ ከወላጅ ወደ ልጅ ሊተላለፍ ይችላል ፤ከእናትም ከአባትም ከእህት እና ውንድም ስኳር በዘር የሚተላለፍ ሲሆን አባት የስኳር ህመም ካለበት የልጅ በስኳር የመታመም እድል በሁለት እጥፍ ይጨምራል።

እህት ወይም ወንድም የስኳር ህመም ካለበት በተለይ ተመሳሳይ መንታ እህት እና ውንድሞች ላይ በስኳር ህመም የመታመም እድል ይጨምራል።

የስኳር በሽታ አይነቶች

1. አይነት 1/በህጻነት እድሜ የሚከሰት ስኳር ህመም

2. አይነት 2/በአዋቂነት እድሜ እና የሰውነት ክብደት አለቅት የጨመሩ ህጻናት ላይ የሚከሰት የስኳር ህመም።

3. ሌሎች አይነቶች (የጨቅላ ህጻናት ስኳር ፣ የተፈጥሮ የስኳር አመንጪዎች ችግር እና የኢንሱሊን ስራ አስተጓጓይ ክስተቶች)

#በዋናነት ሁለት አይነት የስኳር በሽታዎች አሉ።

1. የመጀመሪያው አይነት የስኳር በሽታ፡ በቤተሰብ ውስጥ ካለ የመጠቃት እድል አለ ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን የራሳችን በሽታ ተከላካይ ሴል ኢንሱሊንን የሚያመርተውን ሴል በማጥቃቱና በአንዳንድ ቫይረስ ምክናየት የሚመጣ በሽታ ነው።

• እስከ 45 አመት ባለ የእድሜ ክልል የሚመጣ ሲሆን ኢንሱሊን ባለመኖሩና ባለመመረቱ የሚከሰት ነው።

• 10%ቱን ይይዛል።

2. ሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ፡ ጣፊያ ውስጥ ኢንሱሊን ቢመረትም የተመረተው ኢንሱሊን ጥቅም የማይሰጥና ሰውነታችን የተላመደው በመሆኑ የሚፈጠር ነው።

• ከ45 አመት በኋላ የሚመጣና 90%ቱን የሚይዝ ነው።

• እድሜ መግፋት፡ ውፍረት፡ ንደትና ብስጭት እንደ አነሳሽነት ይቆጠራሉ።

3. በእርግዝና ጊዜ የሚመጣ የስኳር በሽታ ቢኖርም ከወሊድ በኋላ ለብዙዎቹ እናቶች ይጠፋል።

• ይህ የሚሆነው በእርግዝና ወቅት የሚመረት ሆርሞን የኢንሱሊንን መጠን ስለሚቀንስ ነው።

• ከወሊድ በኋላ ሆርሞኑ ስለሚጠፋ ኢንሱሊን ይስተካከላል።

• አይነት አንድ እና ሁለት ስኳር ሲነጻጸሩ

አንድነታቸው፡

የደም የስኳር መጠን ከልክ በላይ መጨመር ሲሆን

.

ልዩነታቸው

1. መንስኤ

- አይነት አንድ በኢንሱሊን ምርት መቀነስ ይፈጠራል

- አይነት ሁለት የኢንሱሊን ምርት በቂ ሆኖ ሳለ የሚጠበቅበትን ያክል አለመስራት (መላመድ) ነው። ይህም የኢንሱሊን ስኳርን ወደ ሰውነት የማስረግ አቅም በመቀነሱ የሚመጣ ነው።

.

2. አጋላጭ ሁኔታዎች

ሀ. አይነት አንድ

በእርግዝና ወቅት ወይም በህጻነት እድሜ በሚከሰት የአንጀት ቫይረስ ተዋህስያን መጠቃት፣ የእንስሳት ወተትን ከስድስት ወር እድሜ በፊት መጀመር።

ለ. አይነት ሁለት

ከልክ በላይ ውፍረት፣ የስኳር ህመምተኛ ቤተሰብ፣ አመገገብ እና የኑሮ ዘይቤ።

.

3. የህመም ምልክቶች የሚታዩበት ጊዜ

ሀ. አይነት አንድ በአጭር ጊዜ ምልክት ያሳያል ስለዚህ በሽታው ጉዳት ሳያደርስ ቶሎ ይታወቃል።

ለ. አይነት ሁለት ረጅም ጊዜ ሳይታወቅ ይቆያል። ይህም በተለያዩ አካላት ላይ ጉዳት ያደርሳል።

.

4. ህክምናቸው ይለያል

ሀ. አይነት አንድ በሰው ሰራሽ ኢንሱሊን መተካት

ለ. አይነት ሁለት በቆሽት የሚመረተው ኢንሱሊን ስራውን አቀላጥፎ በአግባቡ እንዲሰራ አነቃቂ መድሀኒት መስጠት።

#አጠቃላይ የስኳር በሽታ ምልክቶች

• ቶሎ ቶሎ ውሀ መጠጣት

• ቶሎ ቶሎ መሽናት

• ቶሎ ቶሎ የሚመጣ የርሀብ ስሜት

• ክብደት መቀነስ

• የድካም ስሜት

• እይታ ላይ ብጅታና በቀላሉ እጅና እግር መቁሰል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group