Translation is not possible.

#ሰበር

እስራኤል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ስራቸውን እንዲለቁ ጠየቀች

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዳስታወቀው የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ ማክሰኞ እለት ያደረጉት ንግግር ፀብ ጫሪ ነው በማለት ስልጣናቸውን እንዲለቁ እስራኤል ጠይቃለች። ጉተሬዝ የአለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ ጥሰትን በመጥቀስ ባደረጉት ንግግር እና ሃማስ ጥቃቱን የከፈተው ያለ ምክንያት አይደለም ማለታቻው እስራኤልን አስቆጥቷል።

የፍልስጤም ህዝብ ለ56 አመታት በመታፈን ወረራ ተፈፅሞበታል። ነገር ግን የፍልስጤም ህዝብ ቅሬታ በሃማስ የሚደርሰውን አስከፊ ጥቃት ሊያረጋግጥ አይችልም ብለዋል። እናም እነዚያ አሰቃቂ ጥቃቶች የፍልስጤም ህዝብ የሚደርስበትን የጋራ ቅጣት ሊያጸድቁ አይችሉም ሲሉ አክለዋል።

የእስራኤል ቃል አቀባይ ሊዮር ሃይት ለቢቢሲ ራዲዮ 4 ዘ ዎርልድ እንደተናገሩት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊ ንግግር “አንድ ደቂቃ ብቻ በባዶ ቃላት የተሞላ በሃማስ አሸባሪዎች እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ያላወገዘ እንዲሁም “ለሽብርተኝነት ማረጋገጫ” ሰጥቷል ብለዋል። "ከተጎጂዎች ጋር ከመቆም ይልቅ የጅምላ ጭፍጨፋ የደረሰባቸውን ተጎጂዎችን ተጠያቂ አድርገዋል ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ዛሬ ማለዳ እስራኤል በጋዛ ዙሪያ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 16 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ቆስለዋል። የጋዛ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የእስራኤል ጦር በሰሜናዊው ጃባሊያ እና ታል አል-ሃዋ፣ በማእከላዊ ጋዛ በሚገኘው አል-ኑሴራት የስደተኞች መጠለያ ካምፕ እና በደቡብ ካን ዮኒስ የመኖሪያ አካባቢዎችን መትቷል።

{ስምኦን ደረጀ}

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group