Translation is not possible.

#ረሂመሁላሁ የሚለው ዱዓእ ለሞተ ሰው ብቻ ሳይሆን በሂወት ላለም ሰው ይባላል። ነገር ግን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ረሂመሁ ላሁ ከተባለ ፈጥኖ ከአእምሮ የሚደርሰው ያ ግለሰብ ወደአኺራ እንደተሸጋገረ ነው።

ከእለታት አንድ ቀን ከሳዑዱ መገናኛ መንገዶች (ሬድዮ ወይም ቴሌቪዥን ጣቢያ ) በአንዱ ስለ ሸይኽ አቡበክር አልጀዛኢሪይ ወሬ ተነሳ። በመካከልም አንዱ የመረጃው አጠናቃሪ "ሸይኽ አቡበክር ረሂመሁላሁ እንዲህ ብለዋል፤ይሄን ሰርተዋል እያለ ያወራ ነበር።

እናም

ይሄን መረጃ በቀጥታ ሲከታተሉ ከነበሩ የአሜሪካ ሙስሊም ጀመዓዎች መካከል ከፊሎቹ ሸይኽ አቡበክር የሞቱ መስሏቸው ሶላተል ጛኢብ (በሩቅ ለሞተ ሰው የሚሰገድ የጀናዛ ሶላት) ሰግደውላቸዋል። ሸይኽ አቡበክር ግን በሰአቱ በሂወት ነበሩ። በመዲና የነብዩ መስጂድ ትምህርት ይሰጣሉ።

ሸይኽ አብዱልሙህሲን ዓባድ አልበድር ሀፊዘሁላሁ "የሸይኽ አቡበክር አልጀዛኢሪ ትውስታዬ" በሚል ከጻፉት የተወሰደ

Send as a message
Share on my page
Share in the group