Mohammed Amin shared a
Translation is not possible.

ፍልስጥኤማውያን የቅን ሰዎችን ልቦች እያሸነፉ ነው!

ብዙ ሰዎች "እኛ ፍልስጤማዊ አይደለን! ምን አገባን? ደሞስ የኛን ጩኸት ማን ይሰማል?" እያሉ ለግፉአን ማሰማት የነበረባቸውን ድምፅ በገዛ እጃቸው ሲያፍኑ ይታያል።

ነገር ግን በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመን በየትኛውም የዓለም ጥግ ያለ ሰው የሚያሰማው ጩኸት ተደማምሮ የመደበኛውን ሚዲያ አሻጥር ሰባብሮ ህዝብ እያነቃነቀ ነው። ሰፊው ህዝብ ከአሻጥረኛ መንግስታት በላይ መኾኑን በመላው ዓለም በታላቅ ድምፅ እያስተገባ ይገኛል። ከእንግሊዝ እስከ ኮሪያ ፣ ከቦሊቪያ እስከ ስፔይን ፣ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ጎረቤት ኬንያ ድረስ በርካታ የዓለም ህዝብ ከፍልስጥኤማውያን ጎን ቆሟል።

ዛሬ የፂዮናውያን ቅጥረኛ ምዕራባውያን መሠሪ ፖለቲከኞች ብቻቸውን ቀርተዋል። የአየርላንድ ፣ የስፓኝ ፣ የአሜሪካ ሴናተሮች የእስራኤልን ክፋት በፅኑ ኮንነዋል። ስፔን ደፈር ብላ የእስራኤልን መንግስት በአሸባሪነት ከስሳለች። የአየርላንድ ሴናተሮች እስራኤል ሽብርና የጦር ወንጀል እየፈፀመች መኾኑን መንግስታቸው በይፋ እንዲያውጅ ወትውተዋል። አሜሪካዊው አዛውንት በርኒ ሳንደርስ ሳይቀር እስራኤል ግፍ እየፈፀመች መኾኑ በግልፅ ቌንቋ ተናግሯል።

በርካታ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች አይሁዳውያንን ጨምሮ የጺዮናውያንን ፋሺስታዊ አካሄድ በአደባባይ ኮንነዋል። በራሳቸው ሚዲያ ላይ ሳይቀር ቀርበው ሞግተው ረትተዋል። አፍቃሬ ፅዮናዊ ጋዜጠኞች ላይ ህዝብ ተሳልቆባቸዋል።

እስራኤልም በዓለም አቀፍ መድረክ ውርደቷን ተከናንባለች። "ሀማስ አሸባሪ ነው" የሚለው ሙግቷ ውሃ በልቶት እንዲያውም በግልባጩ ዓለም የኔታኒያሁ እና የእስራኤልን መንግስትን አሸባሪነት በግልፅ አስተጋብቷል። እውነት ገሀድ እየወጣ ነው።

አስደናቂው ነገር ግን ፍልስጥኤማውያን ሰፊ ድጋፍና ተቀባይነት ያገኙት ከሙስሊምና ዐረብ ሃገራት ሳይሆን በምዕራብ ሃገራት ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መኾኑ ነው። ጌታህ ስራው ረቂቅ ነው። አንተ ለወንድሞችህ ድምፅህን ብትነፍግ እሱ በመረጠው በኩል ይረዳቸዋል። ከግፉአን ወገን ለመቆም ቢተናነቅህ ከሌላው ወገን ድጋፍ ሲቸረው ታያለህ።

ፍልስጥኤማውያን የቅን ሰዎችን ልቦች እያሸነፉ ነው። የቅን ሰዎችን ልቦች ከማሸነፍ በላይ ምን ድል አለ?

Yunus M. Nassir

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group