Translation is not possible.

የቂያም ቀን 3 ስራዎች ከትልቅነታቸው የተነሳ ሚዛን ላይ

አይገቡም ...

1)ለሰዎች ይቅርታን ማድረግ ( ﺍﻟﻌﻔﻮ ﻋﻦ ﺍﻟﻨﺎﺱ )

* ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆነ ወሰን አልተሰጠውም..

አላህ ﷻ እንዲህ ይላል ...

ﻓَﻤَﻦْ ﻋَﻔَﺎ ﻭَﺃَﺻْﻠَﺢَ ﻓَﺄَﺟْﺮُﻩُ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ

" ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው

... "

2) ሰብር ( ﺍﻟﺼﺒﺮ )

* ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆነ ወሰን አልተሰጠውም..

አላህ ﷻ እንዲህ ይላል ...

ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﻳُﻮَﻓَّﻰ ﺍﻟﺼَّﺎﺑِﺮُﻭﻥَ ﺃَﺟْﺮَﻫُﻢ ﺑِﻐَﻴْﺮِ ﺣِﺴَﺎﺏٍ

" ታጋሾች ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው።"

3) ፆም ( ﺍﻟﺼﻴﺎﻡ )

ረሱል ﷺ አሉ

አላህ ﷻ እንዲህ አለ:-

ﻛﻞ ﻋﻤﻞ ﺍﺑﻦ ﺁﺩﻡ ﻟﻪ ﺇﻻ ﺍﻟﺼﻮﻡ ﻓﺈﻧﻪ ﻟﻲ ﻭﺃﻧﺎ ﺃﺟﺰﻱ ﺑﻪ .

"ሁሉም የአደም ልጅ ስራ የርሱ ነው

ከፆም በስተቀር ፆም የኔ ነው እኔም ነኝ ምንዳውን

የምመነዳው።"

{ ቡኻሪና ሙስሊም }

* ምንዳቸው ምን ያህል እንደሆነ ወሰን አልተሰጠውም..

የቂያም ቀን ተጣሪው የታሉ ምንዳቸው በአላህ ላይ

የሆነው ሲል ይጣራል ...

* ፆመኞች

*ታገሾችና

*ይቅር ባዮችን ብቻ ይቀበላቸዋል።

እኔንም እናንተንም በዚህች ጥሪ ከሚጠሩት አላህ

ያርገን!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group