Translation is not possible.

ጠያቂ፡- የተከበሩ ሸይኽ! የቁርኣን አንቀፆችን ግድግዳ ላይ ማንጠልጠል ምንድን ነው ብይኑ?

ኢብኑ ዑሠይሚን፡ ለምንድን ነው የቁርኣን አንቀፆችን ግድግዳ ላይ የምናንጠለጥለው?

ጠያቂ፡ ለጌጥ!

ኢብኑ ዑሠይሚን፡ ለውበት ከሆነ እንግዲያው (ይህን የሚያደርገው) የአላህ አንቀፆችን መቀለጃ አድርጎ ይዟቸዋል ማለት ነው!! እንዴት ተብሎ በልብ ውስጥ ላለ ህመም ፈውስ ሆኖ እንዲሁም መገሰጫ ሆኖ የወረደው የተከበረውና ታላቁ ቁርኣን ለግድግዳ ማስጌጫ ይውላል?!!

ጠያቂ፡- ለበረካ ፍለጋ ከሆነስ?

ኢብኑ ዑሠይሚን፡ ቀደምቶች በንዲህ አይነት ተግባር በረካን ይፈልጉ ነበርን? ማስረጃስ መጥቷል? መልሱ፡- “በጭራሽ አልመጣም” የሚል ነው፡፡ እኛ ዘግይተን የመጣን ትውልዶች ቀደምቶቻችንን የበቃቸው ሊበቃን ይገባል፡፡ ሶስተኛ ምክኒያት ካለ አምጣ

ጠያቂ፡- (የሚያነቡትን ሰዎች) ለማስታወስ

ኢብኑ ዑሠይሚን፡- አንቀፆቹ የሚለጠፉበት ግድግዳ አካባቢ የሚቀመጡ ሰዎች አይተው ያስታውሳሉ? ቀድሞ ነገር ያነባሉ? መልሱ “በጭራሽ!” የሚል ነው፡፡ ምናልባት ጥቂት ካልሆኑ በቀር፡፡ ያውም ከኖሩ ነው፡፡ አራተኛ ምክኒያት ካለ አምጣ

ጠያቂ፡- ከጂን ለመጠበቅ

ኢብኑ ዑሠይሚን፡- መልካም ቀደምቶቻችን በእንዲህ አይነት ተግባር ከጂን ይጠበቁ እንደነበር ማስረጃ መጥቷልን?

ጠያቂው፡- የለም!

ኢብኑ ዑሠይሚን፡- በፍፁም! ስለዚህ እንዴት ሆኖ ነው ይሄ ዘዴ ከቀደምቶቻችን ተሰውሮ ለኛ የተገለጠልን?!!

ስለዚህ ይህን በተመለከተ የምንለው ነገር ቢያንስ ቢያንስ “ቢድዐ ነው!” የሚል ነው፡፡ ይህ እንግዲህ በሆነ መልኩ የቁርኣንን ክብር የሚያዋርድ ከመሆኑ ጋር ነው፡፡ ምክኒያቱም ለምሳሌ የሆነ ገፅ ላይ ወይም ግድግዳ ላይ ((ከፊላችሁ ከፊላችሁን አይማ)) (አልሑጁራት፡ 12) የሚል ይፃፋል፡፡ ስብሰባው ግን በሃሜት የተሞላ ይሆናል፡፡ ይሄ ሹፈት ነው!!

ስለዚህ ግድግዳም ላይ ይሁን ወረቀት ላይ ወይም ሌላ ነገር ላይ የቁርኣን አንቀፆችን ፅፎ ግድግዳ ላይ አንጠልጥሎ ያገኛችሁትን ሁሉ ከዚህ ተግባር እንዲታቀቡ ምከሯቸው፡፡ የአላህ ንግግር ለዚህ ተግባር መገልገል አይቻልም” በለው ወንድምህን፡፡…

(ሊቃኣቱልባቢልመፍቱሕ፡ 25/197)

ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡ ጥፋቱ ከብዙ ቤቶች ውስጥ ያለ ነውና ሰዎችን ከጥፋቱ ለመመለስ ያቅሞትን ይጣሩ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group