Translation is not possible.

•አንዳንድ ወዳጆች አሉ… አንተን እንደራሱ የሚወድ፤ ምናልባት ከራሱም የሚያስበልጥህ፡፡ በሁሉ ነገር የቅርብህ ነው፣ ብታጠፋ ዝም አይልህም፣ ብትሳሳትም አይስቅብህም፣ ጥሩ ባትሆን እንኳ ያስተካክልሃል እንጂ በሌላ አይቀይርህም፡፡

• አንዳንድ ወዳጆች አሉ…ስሜትህን የሚረዳልህ፣ ብሶትህን የሚያዳምጥልህ፣ እንባህን የሚጠርግልህ፣ እጅህን ይዞ የሚያነሳ ወዳጅ…

• አንዳንድ ወዳጆች አሉ… ቅድሚያ ላንተ ይሰጣል፣ ጉዳዬ አንተ ነህ ይላል፣ አንዳንዴ ከነፍስህ ጭምር ቀድሞ ይደርስልሃል፣ ነፍስህ በመጥፎ ስታዝህ እሱ በመልካም ነገር ያዝሃል።

• አንዳንድ ወዳጆች አሉ… በቃል ሳይሆን በተግባር ስላንተ ብዙ ይሆናል፣ ከዕረፍቱ በፊት ላንተ ማረፍ ይጨነቃል፤ ባንተ መደሰት ይደሠታል፣ ባንተ መብላት መጠጣት ይረካል፣ ስላንተ እያሰበ ያለ እንቅልፍ ያድራል ፡፡

⇛ትንሽ ያጋነንኩ ይመስላል አይደል!? አይ! አላጋነንኩም። የዚህ ዓይነት ወዳጆችም አሉን ―አልሐምዱ ሊላህ― ለሰው ብቻ የሚኖሩ፣ ስለሰው የሚጨነቁ። አላህ ይጠብቅልን!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group