Translation is not possible.

የተባበሩት መንግሥታት 35 ሠራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት ገለጸ!

ጄይሉ ቲቪ ጥቅምት 13/2016

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 35 ሠራተኞች ጋዛ ሰርጥ ውስጥ እንደተገደሉበት አስታወቀ።የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጥኤም ስደተኞች ኤጀንሲ ስድስት ሠራተኞች ባለፉት 24 ሰዓታት መገደላቸውን ገልጾ፣ በአጠቃላይም በባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ 35 የድርጅቱ ሠራተኞች ተገድለዋል ብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ "በህልፈታቸው አዝነናል እናም በዚህ ወቅት የተቸገሩትን ለመርዳት እየጣሩ ካሉ የሥራ ባልደረቦቻችን ጋር አብረን እንቆማለን" ሲሉም በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያደረገችው ያለው ወታደራዊ ዘመቻ ወራት ሊፈጅ እንደሚችል አስታውቃ፣ የአየር ጥቃቷንም አጠናክራ ቀጥላለች።

በእነዚህ ጥቃቶች ከተገደሉት አብዛኞቹ ሕጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ከጋዛ የጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።ከተገደሉት መካከል 2,055 ሕጻናት፣ 1,119 ሴቶች፣ 217አረጋውያን እንደሚገኙበት ተገልጿል። በአጠቃላይ የተገደሉ ሰዎች ከ5 ሺህ አልፏል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group