ስለጋዛና ፈለሰጢን ሳስብ የሚታየኝ የአላህ ዝም ማለት ሳይሆን የኛ ስንፍናና የቤት ስራችንን በአግባቡ አለመስራት ነው። የፍልስጤም ህዝብ እንደህዝብ መክፈል የሚጠበቅበትን መስዋዕትነት ከፍሏል። እኛ ግን ከትናንት እስከዛሬ ስንናቆር፣ በየማህበራዊ ሚዲያው ስንዘላለፍ፣ እርስ በእርስ ስንጠላለፍ የረባ ስራ ሳንሰራ እንቆይና ይሄ ሲመጣ እናለቃቅሳለን።
አላህ በቁርአኑ ተዘጋጁላቸው ሲለን የምንዘጋጀው ባለው የስልጣኔ ልክ እንጂ በጦር መሳሪያ ብቻ አይደለም። እያንዳንዱ የሙስሊም ሀገር ቴክኖሎጂ በእነርሱ እየተመራ ሀገራቱ ነፃ ናቸው ማለት ይከብዳል። ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የምርምርና የጥናት ተቋማት የሉንም። ችግሮቻችንን የምንፈታበት የምርምር ተቋም የለንም። እስልምና ውስጥ ያሉ ጉዳዮችን እንኳ በቀደሙት ሸሆች ምርምር ላይ ተወስነናል። ይደክማል 😔
የተማረ የሰለጠ የሰው ሃይል የለንም። ወጣ ብሎ የሚያስብ ጭንቅላት የለንም። የምድር ቆይታችን የአላህን ባህሪ ተላብሶ ምድርን ማስተዳደር መሆኑን ዘንግተናል። በዚህ ሁሉ ውስጥ የኛን ሸክም የተሸከሙት ፍልስጢኖች እንዲህ ቢሆኑ አላህን ዝም አልክ የማለት ሞራሉ አለን ወይ 🥺