Translation is not possible.

"አንቺ  ጀግና ሴት ነሽ"

---------------------

አንቺ ጀግና ሴት ነሽ ፍፁም የበረታሽ፡

ውስጥሽ ያለን ህመም ለብቻሽ የረታሽ፡

ሌላ የማይችለው ከሰው ያልደረሰ፡

ስቃይ ቁስል አዝለሽ ልብሽን ያራሰ፡

አሏህ ያውቃል ብለሽ በፅናት ቆመሻል፡

ኸረ ለአንች አይነቷስ ክብር ይገባሻል፡

እጅሺን ያልሰጠሽ ለህይዎት ፈተና፡

እውነትን ያለቀቅሽ ለውሸት ትንተና፡

የመከራን ጂረት ወንዞችን ተሻግረሽ፡

የበደል ዕልፍ እሾህ በልብሽ አኑረሽ፡

ከህይወት ገጠመኝ ትዕግስትን ተምረሽ፡

ከዛሬ የደረሽ አዎ አንቺ ነሽ ጀግና፡

መልካምነት እንጂ የለሽም ብልግና፡

ሰው ቀርቦ ቢሸሽም እምነትሽን ቢያጎል፡

እቅድና ተስፋሽ የማይስተጓጎል፡

አጨለምናት ሲሉ ፈክተሽ የምትደምቂ፡

አስለቀስናት ሲሉ ንቀሽ የምትስቂ

በፅናት አቋም ላይ የምትታወቂ፡

ማለፍ የምታውቂ ሁሉን ፈገግ ብለሽ፡

ከሴትነት ሚዛን ምንም ያልጎደለሽ፡

ለጠላት ለወዳጅ ጥሩ አሳቢ ሆነሽ፡

ምስክር ነኝ እኔ አንቺ  ጀግና ሴት ነሽ፡

         በኑረዲን አል አረብ

Send as a message
Share on my page
Share in the group