Перевод невозможен

🍀ትልቅ ብሥራት!🍀

~

ለአንድ ወንድምህ ብድር አበድረህ በሆነ የጊዜ ገደብ እንዲመልስልህ ብትስማሙ

🎈 ካበደርክበት ጊዜ አንስቶ እስከተስማማችሁበት ጊዜ ድረስ በገንዘቡ ልክ በየቀኑ እንደምትሰድቅ ይታሰብልሀል።

🎈 የጊዜ ገደቡ ተጠናቆ "ሌላ ጊዜ ስጠኝ" ቢልህና ብትስማማ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ደግሞ በየቀኑ በመጠኑ ሁለት እጥፍ እንደምትሰድቅ ይቆጠርልሀል።

ማስረጃውስ?

~~~~

🛑 ሶሐባው ቡረይዳ ረዲየላሁ ዐንሁ ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ﷺ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል: –

(مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا فَلَهُ بِكُلِّ يَوْمٍ مِثْلِهِ صَدَقَةٌ)

"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው።"

🛑 ከዚያም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ:–

"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው።"

በዚህን ጊዜ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ‘ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው’ ስትል ሰምቼህ ነበር። ከዚያ ደግሞ ‘ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ለሱ በየቀኑ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው’ ስትል ሰማሁህ?" አልኳቸው።

🛑 እሳቸውም እንዲህ አሉ: –

"የእዳው መክፈያ ጊዜ እስከሚደርስ ድረስ ለሱ በየቀኑ አምሳያውን ሶደቃ አለው። ጊዜ ገደቡ ደርሶ ተጨማሪ ጊዜ ከሰጠው ደግሞ ለሱ በየ እለቱ ሁለት አምሳያውን ሶደቃ አለው።"

📚 ኢማሙ አሕመድ የዘገቡት "ሶሒሕ" ሐዲሥ ነው።

ከዚህም የበለጠውን ደግሞ ተመልከት!

ከአቢል የሰር ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል: –

( مَنْ أَنْظَرَ مُعْسِرًا أَوْ وَضَعَ عَنْهُ أَظَلَّهُ اللَّهُ فِي ظِلِّهِ )

"ችግረኛን ጊዜ የሰጠ ወይም የተወለት አላህ በጥላው ስር ያስጠልለዋል።"

📚 ሙስሊም ዘግበውታል።

Отправить как сообщение
Поделиться на моей странице
Поделиться в группе