Translation is not possible.

📗 ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- "በቀን ውስጥ ለመቶ ጊዜ ያህል…

➡️ ሱብሐነላሂ ወቢ ሐምዲሂ ⬅️ ያለ ሰው፡ ኃጢአቱ እንደ ባሕር ዐረፋ የበዛ ቢኾንም ይሰረዛል”። 📗(ቡኻሪይ 6042)

2️⃣ ንግግሮች ለምላስ የሚቀሉ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አረሕማን ዘንድ የተወደዱ ቃላት ናቸው… ➡️ ሱብሐነላሂ ወቢ ሐምዲሂ - ሱብሐነላሂል ዐዚም ⬅️ 📗(ቡኻሪና ሙስሊም)

➡️ ሱብሐነላሂ ወቢ-ሐምዲሂ ⬅️ ሲያነጋም ሆነ ሲያመሽ ይህን ዚክር 100 ጊዜ ያለ ሰው የቂያም ቀን እሱ ያለውን ያህል ወይም የበለጠ ያለ ሰው እንጂ ከሱ የተሸለ መልካም ስራ ይዞ የሚመጣ የለም። 📗(ሙስሊም 2692)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

⭕️ በማንኛውም ቦታና ሰዓት አላህን ማውሳት ይቻላል፡፡ በተለይ ደግሞ በንጋትና በምሽቱ የሚባሉ ዚክሮች! ኃጢአትንም ያብሳሉ፡፡ ይህን ከሚያሳዩ ሐዲሦች መካከል ቀጣዩን እንመልከት፡-

📗 ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- "ወደ መኝታው ሲመጣ፡-

➡️ ላ ኢላሀ ኢልለሏህ፡ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፡ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምድ፡ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር፡፡ ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላሂል ዐሊዪል ዐዚም፣ ሱብሐነላሂ ወል-ሐምዱ ሊላህ፣ ወላ ኢላሀ ኢልለሏሁ ወላሁ አክበር ⬅️

ያለ ሰው፡ ኃጢአቱ እንደ ባሕር ዐረፋ የበዛ ቢኾንም ይቅር ይባላል።

📗(ሶሒሑ ተርጊብ ወትተርሂብ 607፡አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📗 ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- 1️⃣0️⃣ ጊዜ፡-

➡️ ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ። ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ⬅️

☀️ ንጋት ያለ በእሷ ምክንያት አንድ መቶ ምንዳዎች ተጽፎለታል፡፡ ከእርሱ ላይም አንድ መቶ ሐጢአቶች ተሰርየውለታል፡፡…

አንድ ጫንቃን ነጻ ከማውጣት ጋር ትስካከልለታለች፡፡ በእሷ ምክንያትም በዚያን ወቅት እስከሚያመሽ ድረስ ይጠበቃል፡፡

🌖 ይህንኑ ሲያመሽ ያለ የዚሁ ዓይነት ይሆንለታል”።

📗 (ሐዲሡን አሕመድ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (8719) ላይ ዘግበውታል፡፡ ኢብን ባዝም (አላህ ይዝንላቸው) ዘገባው በመልካም ደረጃ የሚገኝ መሆኑን አረጋግጠዋል)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📗 ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

➡️ አላሁመ አንተ ረቢ፣ ላኢላሀ ኢልላ-አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአና-ዐብዱከ፣ ወአና ዐላ-ዐህዲከ ወወዕዲከ መስተጠዕቱ፣ አዑዙ-ቢከ ሚን-ሸሪ ማሰነዕቱ፣ አቡኡ-ለከ ቢኒዕመቲከ-ዐለየ፣ ወአቡኡ-ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር-ሊ፣ ፈኢንነሁ ላየግፊሩ-ዙኑበ ኢልላ-አንተ ⬅️

💬አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፣ ካንተ ሌላ አምላክ የለም፣ እኔ አንተ የፈጠርከኝ ባሪያህ ነኘ፣ በቻልኩት ያህል በቃል-ኪዳንህና በተስፋህ ስር ነኝ፣ ከፈጸምኳቸው ክፋቶች ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልክልኝን ጸጋዎች አምናለሁ፣ ኃጢአተኛ መሆኔንም አምኛለሁ፣ ኃጢአትን ካንተ ውጭ የሚምር የለምና እባክህ ማረኝ»።

ይህንን ኢስቲግፋር በእርግጠኝነት አምኖበት በቀኑ ክፍል ያለ ሰው ከመምሸቱ በፊት ቢሞት የጀነት ነው፡፡ ልክ እንደዛው በለሊቱም ክፍል ብሎ ከመንጋቱ በፊት ቢሞት የጀነት ነው። (ቡኻሪይ 6306)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📗 ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- 

"ከፈርድ ሶላት ኋላ አላህን 33 ጊዜ ‹‹ሱብሐነላህ››፣ 33 ጊዜ ‹‹አል-ሐምዱ ሊላህ››፣ 33 ጊዜ ‹‹አላሁ አክበር›› በማለት በጥቅሉ 99 ጊዜ ያለና በመቶኛውም…

‹‹ላ ኢላሀ ኢልለሏህ፡ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ፡ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምድ፡ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር››

በማለት ያወደሰው ሰው፡ ኃጢአቱ እንደ ባሕር ዐረፋ የበዛ ቢኾንም ይቅር ይባላል”። 📗(ሙስሊም 1380)

📗 በምድር ገጽ ላይ ኾኖ፡-  ➡️ ላ ኢላሀ ኢልለሏህ፣ ወላሁ አክበር፣ ወሱብሐነሏሂ ወል-ሐምዱ ሊላህ፣ ወላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ ⬅️…

የሚል ሰው የለም፡ አላህ ኃጢአቱን ከባሕር ዐረፋ የበዛ እንኳ ቢሆን የማረው ቢኾን እንጂ!”። 📗(ነሳኢይ 10658)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📗በየቀኑ ሲያነጋም ሆነ ሲያመሽ 7️⃣ ጊዜ ይህንን ዚክር ያለ ሰው የዱንያውንና የአኼራውን ሃሳብ አላህ ይሸፍንለታል

➡️ ሐስቢየላሁ ለኢላሀ ኢላ ሁው፣ ዐለይሂ ተወከልቱ ወሁወ ረቡል-ዐርሺል ዐዚም ⬅️ 📗(ነሳኢይ ዐመሉል-የውሚ ወል-ለይላህ 71)

📗ማንኛወም የአላህ ባሪያ በየቀኑ ጠዋትና በየምሽቱ 3 ጊዜ፡-

➡️ ቢስሚልላሂ- ልላዚ ላ የዱርሩ መዐ-ስሚሂ ሸይኡን ፊልአርዲ ወላ ፊስሰማኢ ወሁወ- ስሰሚይዑ-ልዐሊይም ⬅️…

በዚያ ከስሙ ጋር በምድር ወይም በሰማይ ላይ ያለ አንዳች ነገር የማይጎዳው በሆነው አላህ ስም፡፡ እርሱም ሰሚውና ዐዋቂው ነው፡፡ ሶሰት ጊዜ ካለ አንዳች ነገር አይጎዳውም፡፡

📗(ሐዲሡን አሕመድ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (446)፣ አት-ቲርሚዚይ በቁጥር (10179)፣ ኢብን ማጀህ በቁጥር (3869)ላይ ዘግበውታል)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📗 እናታችን ጁወይሪያህ ቢንቲል ሓሪሥ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ባስተላለፈችው፣ በአንድ ወቅት ነብዩ ﷺ ሱብሕን ከሰገዱ በኋላ ማለዳ ላይ ከሷ ዘንድ ወጡ…

  እሷ መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ ዚክር ላይ ነች። እዚያው እንደተቀመጠች ረፋድ ላይ ተመለሱ…

"ካንቺ ከተለየሁ ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተለየሁብሽ ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽም?" አሏት። "አዎ" አለች...

በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ፡-

"በእርግጥም ካንቺ በኋላ አራት ንግግሮችን ሶስት ጊዜ ተናግሬያለሁ። ከንጋት ጀምሮ አንቺ ካልሺው ጋር ቢመዘኑ (እኔ ያልኳቸው) ይመዝናሉ፡-

* ሱብሓነላሂ ወቢ ሐምዲሁ ዐደደ ኸልቂሁ፣

* ወሪዷ ነፍሲሂ፣

* ወዚነተ ዐርሺሂ፣

* ወሚዳደ ከሊማቲሂ።" 📗(ሙስሊም የዘገቡት)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📗 አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- 

"‹‹ጋሻችሁን ያዙ!›› ፡- ‹‹የመጣ ጠላት አለ እንዴ?›› አንቱ የአላህ መልክተኛ? ስንላቸው፡-

‹‹አይ! ከእሳት የምትከላከሉበትን ጋሻችሁን! ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር በሉ፡፡…

እነሱም የቂያም ቀን ለባለቤታቸው ከእሳት አትራፊ ሆነው ይመጣሉ…"  📗(ሐኪም አል-ሙስተድረክ)

📗 ረሱል ﷺ ከጀነት ድልብ ሃብቶች ውስጥ እንደሆነ የገለፁት የዚክር አይነት፡-

➡️ ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ" ⬅️ 📗(ኢብኑ ሒባን)

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

⭕️ እነዚህ ምሳሌዎች  ናቸው። ሌሎችም ብዙ አሉ። ከነዚህ በተጓዳኝ ከውዱእ በኋላ፣ ከአዛን በኋላ፣ መስጂድ ስትገባ፣ ከመስጂድ ስትወጣ፣ ከሶላት በኋላ፣ ከምግብ በኋላ፣ ስትተኛ፣ ስትነሳ፣ ወዘተ ያሉትን ብትል ቆጥረህ የማትዘልቀው አጅር አለህ

በጥቅሉ ጊዜያቹን መድባቹ ዚክርን የሂወታቹህ አካል አድርጉት። ዚክር ትኩረት እንጂ የረባ ጥረት አይጠይቅህም። ረሱል ﷺ እንዳሉት "ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ”።

🤲 “ጌታችን ሆይ! አንተን ለማስታወስ፣ አንተን ለማመስገን እንዲሁም አንተን ባማረ መልኩ ለመገዛት አግዘን፡፡”

🔹🔹🔹🔸🔸🔸

📨  ይህን መልእክት ለእህት ወንድሞች ሼር ያድርጉላቸው፣ ወደ ቅን መንገድ የተጣራ ሰው፣ የተከተሉት ሰዎች ሁሉ የሚያገኙት አጅር ምንም ሳይጎድልባቸው ለሱም ይኖረዋል…" (ቡኻሪና ሙስሊም)

አላህ ከሚጠቀሙት ያድርገን!!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group