Translation is not possible.

🌎 *كما يقولون الدنيا دوارة … !!*

ዱንያ ተሽከርካሪ ናት እንዲሉ አባባሉ

ኢብኑ ከሲር አልቢዳየቱ ወኒሃያህ በተሰኘው ኪታባቸው ይህን አስፍረው ሳይ አጂጂብ አልኩ

ነገሩ እንዲህ ነው

ከየመን ነገስታት ቤተሰብ የነበረው ዋኢል ኢብኑ ሁጅር አልሐድረሚይ እስልምናውን እያወጀ ወደ አላህ መልዕክተኛ (صلى الله عليه وسلم) ዘንድ መጣ መልዕክተኛው (صلى الله عليه وسلم) እሱ ከመድረሱ በፊት ቀሪ የነገስታት ልጅ ይመጣችሇል     ብለው ተናግረው ነበር ።

ዋኢልም ሲመጣ የአላህ መልዕክተኛ (صلى الله عليه وسلم)  የሚማርከው ፈገግታቸው እንኳን ደህና መጣህ ብለው አቀረቡት ብሎም ትቶት ለመጣው ንግስና ና መሪነት ካሳ ይሆነው ዘንድ መሬት ሰጡት ሙዓዊያህ ኢብኑ አቡ ሱፍያንንም የተሰጠውን መሬት ያሳየው ዘንድ አብረው ላኩት ሙዓዊያህ ያን ግዜ ድህነቱ ከመበርታቱ የተነሳ የሚጫመተው ጫማ እንኳ ስላልነበረው ሞቃታማው መሬት እግሩን ይፈታተነው ይዟል ።

ታዲያ  አብረው ለዋኢል ወደ ተሰጠው መሬት እየሄዱ ሳለ ሙዓዊያ ለዋኢል እባክህ ግመሏ ላይ ከጀርባህ እንድሳፈር ፍቀድልኝ ይለዋል ዋኢልም ለግመሉ ሰስቼ ሳይሆን አንተ ከንጉስ ጀርባ መፈናጠጥ የማትችል ሰው ስለሆንክ አይሆንም ይለዋል ሙዓዊያም እንግዲያውስ ጫማህን ስጠኝ ይለዋል ዋኢልም ለጫማው ሰስቼ ሳይሆን አንተ የንጉስን ጫማ መልበስ የማትችል ስለሆንክ አይሆንም ነገር ግን በግመሏ ጥላ ስር ሂድ አለው ።

ከዛም አላህ ዘመንን ያዞረው ጀመር አመታት ተቆጠሩና የሙስሊሞቹ ኸሊፋህ ዑመር አልፋሩቅ ሙዓዊያን ሻም ላይ አሚር አድርገው ሾሙት ዋኢልም እድሜያቸው ሰማኒያዎቹን ከተሻገሩ በሇላ ወደ ሻም መተው ሙዓዊያ የንግስናው ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ሳለ ወደ ሙዓዊያ ገቡ ሙዓዊያም ዋኢልን ሲያዩ ከመቀመጫው ወርደው ዋኢልን በቦታው አስቀመጡና በፊት በመካከላቸው ስለተከሰተው ነገር አወጓቸው ገንዘብ እንዲሰጠውም አዘዙላቸው ዋኢልም ገንዘቡን ከኔ በላይ ይበልጥ ተገቢ ለሆነ ሰው ስጥ ነገር ግን ያኔ ባየውት ትግስትህ አላህ ዘመኑን ወደሇላ መልሶት ከፊቴ ባስቀምጥህ ወደድኩ አሉ  ። 

📕 البداية والنهاية : ج 5

     

‼ *لا غنىٰ يدوم ولا فقر يبقىٰ ، اقتصد في علاقاتك وتعاملاتك ، فالدنيا دوارة* !!!

እዚች ተሽከርካሪ በሆነች ዱንያ ላይ ዘውታሪ የሆነ ሀብት የማይወገድ ድህነት የለምና ከሰዎች ጋር ያለህን ግንኙነት የተስተካከለ አድርግ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group