Translation is not possible.

🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻

📜ለባለትዳሮች ብቻ…

|•| የባልና ሚስት የሀላል ፍቅር ጨዋታ በግጥም

ባል:

አንቺ የኔ ፍቅር የህይወት ጨረቃ

ልቤ ይከፋዋል ሳጣሽ ለደቂቃ

ሴቶች ብዙ ናቸው አንቺ ግን ልዩ ነሽ

ህይወቴን አድሻት ካጠገቤ ሁነሽ

ሚስት:

አንተ የኔ ፍቅር የህይወት ነፀብራቅ

ፍቅርህ ምግቤ ነው ከጎኔ አትራቅ

ወንዶች ብዙ ናቸው አንተ ግን ልዩ ነህ

ፍቅርህን መግበኝ ካጠገቤ ሁነህ

ባል:

የትዳር አጋሬ የልጆቼ እናት

ደስታዬ አለሜ የሀላል ሚስቴ ናት

ጌታዬ ይመስገን እሷን አድሎኛል

ውዴን የመሰለ ከቶ የት ይገኛል

ሚስት:

የልጆቼ አባት የትዳር አጋሬ አጋር

ተስፋዬ ብሩህ እስካለሁ ካንተ ጋር

መኖርህ መኖሬ መጥፋትህ መጥፋቴ

ሳጣህ ቅር ይለኛል አትጥፋ ከፊቴ

ባል:

የሽቶ መኣዛ የቴምር ጭማቂ

ሁቢ ማር ወለላ ሁሌም ተናፋቂ

ጣፈጭ ነገር ሁሉ አንቺን ይመስሉኛል

ብቻ ምን ልበልሽ… ቃላቶች ያጥሩኛል!

ሚስት:

የዐይኔ ማረፊያ የህይወቴ ፀደይ

የፊትህ ብርሃን ይበልጣል ከፀሐይ

የረህማን ፅጦታ የጀሊሉ ኒዕማ

አንጀቴ ይርሳል ድምፅህን ስሰማ

ባል:

ሚስቱን የሚመታ የትዳር አጋሩን

የፍቅር አይደለም ሳስበው ነገሩን

ውዷ ባለቤቴ ክብርሽ ይከበር

አንቺን የመታው ቀን እጄ ይሰበር

ሚስት:

እኔ እንክት ልበል እኔ ልሰባበር

እሾህ አይውጋብኝ እንኳንስ መሰበር

የፍቅር አርበኛ ፊትአውራሪ ጀግና

አንተ መውድድ እንጂ ዱላ መች ታውቅና

ባል:

አኔ እዚህ ጎራ አንቺ ወዲያ ማዶ

ልቤ አረረልሽ በፍቅርሽ ማገዶ

የልቤ በረዶ መዳኒቴ ነሽ

ውዷ ባለቤቴ ሁቢ እንዴት ነሽ?

ሚስት:

ፈረስ አይጋልበው በበቅሎ አይደረስ

በርሬ አንዳልመጣ ያለህበት ድረስ

ውዱ ባለቤቴ ፍቅርህ ለበለበኝ

አሁንስ ከብዶኛል በዱኣህ አስበኝ

N.B―ታሳቢነቱ በሩቅ ተነፋፍቀው ላሉ የትዳር ጥንዶች ነዉ

ነዉ አሉ

🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻🪻

Send as a message
Share on my page
Share in the group