Translation is not possible.

#እህቴ_ሆይ!!

     #ቃልሽ_ተግባር ይሁን!!

〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

ምኞቴ ሱንዩን፣ እያልሽ ታወሪያልሽ፣

ሚዲያ ላይ ውብ ነው፣   ቃላት ፕሮፋይልሽ፣

ከ online ጀርባ፣ ሲታይ ተግባርሽ፣

ዱርየው ጫት ቃሚው፣ ሹፌሩ ነው ምርጫሽ!!

ከላይ ኒቃብ ጅልባብ፣ አክለምልመሽ ለብሰሽ፣

ባለ-ቃሪያ ሱሪው፣ ከሱ ጋር ነው ውሎሽ!!

ቢሾፍ ቢፌዝበት፣ ጅልባቡ ኒቃብሽ፣

ክብር ጭንቀት የለው፣ ቅንጣትም ለዲንሽ፣

ከቶም የሚያወራ፣ ሁሉን ስለ ነውርሽ፣

ከሱ-ጋር አሙቀሽ፣ መንገድ ትስቺያለሽ፣

ያልሆነ እየሰራሽ፣ ዲን ታሰዲቢያለሽ፣

በዚህ ሁሉ ነገር፣ ትጠየቂያታለሽ!!

ሚዲያ አጨናንቀሽ፣ ሀላል ሀላል ብለሽ፣

ሀላል የሚጠላው፣ ሆኗል ሚስጥረኛሽ፣

ጃሂል ነው በሚል ስም፣ ዑዝር እየሰጠሽ፣

ያሻውን ቢሰራ፣ አብረሽ ትሰምጫለሽ፣

ጫት አስካሪ መጠጥ፣ ሳይቀር ትጋሪያለሽ!!

ሱና ሚያከብረውን፣ ባዳ ታደርጊያለሽ፣

ያንገሸግሽሻል፣ በርቀት እያስጠላሽ!!

ላውን ፀዳሽ እንጅ፣ ተመርዟል ልብሽ!!

ዲኑ-ነው መስፈርቴ፣ እያልሽ ለፍፈሽ፣

ቤትና መኪና፣ እሱ ነው ታርጌትሽ!!

ጽኑ ነኝ በሱና፣ ብለሽ ተደናፍተሽ፣

ሂዝብይ አይነካኝም፣ እያልሽ ተኩራርተሽ፣

ቢድዕይ ሲመጣ፣ አንቺ ኒካህ ላይ ነሽ፣

ሁሉንም እህቶች፣ ባንቺ ባታስወቅሽ፣

እንዲህ የምትሰሪ፣ ስንት አይነት ሴት አለሽ፣

መዘዙ ብዙ ነው፣ እህቴ ይቅርብሽ፣

ቃልሽ ተግባር ይሁን፣ ፍሬ ታፈሪያለሽ!!

🌹🌹🌹👇👇

Send as a message
Share on my page
Share in the group