Translation is not possible.

ቢስሚላህ!

ትሰማለህ? ማንነትህን ለሌሎች ለማብራራት አትዳክር።አንተ በተለያዩ ሰዎች አስተሳሰብ የተለያየ ስብዕና ነህና።ዋናው ነገር በራስህና በአምላክህ መካከል ያለውን ግንኙነት በተቻለህ ሁሉ ለማስተካከል ሞክር።ከዝህ ባለፈ አንተም ሆንክ ሌሎች የፈጣሪ ባሮች ናችሁ።በተለይ በሕይወት አጋጣሚ በቂ ጊዜ ከአንተ የማሳለፍ እድል ኖሯቸው ነገር ግን ብዙ ነገሮችህን እንደማያውቁና ከማያውቁህ ተርታ ሆነው ራስህን ዳግም difine እንድታደርግላቸው የሚፈልጉትን አሽቀንጥረህ ጣልና ጉዞህን ቀጥል።ትክክለኛ ወዳጅህ ማለት ስትሳሳት ከማኑም ቀድሞ የሚገስፅህና ከስህተትህም የሚመልስህ ሲሆን፣አስመሳይ ወዳጅህ ግን አንተ ፊት መልካም፣ዞር ሲል ግን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ አንተን ለመዘቅዘቅ የሚታትር ነው።ባሪያነትህ ለፈጠረህ አምላክህ እንጂ በዝህች ምድር አንተ ሎሌው እንድትሆን የተፈረደለት ማንም የለምና ለጌታህ እንጂ ለማኑም አታጎንብስ።ብታጎነብስም ከመጉደፍ ያለፈ አላህ ከፃፈልህ ውጭ ምንም ስለማታገኝ።የአር-ረ-ህማን ባሪያ ብቻ መሆንህን ስታስብ ግን ሁሌም አንገትህን ቀና አድርግና አልሀምዱሊላህ በል።

ዱንያ ብቻህን ሆነህ የመጣሃት ለብቻህም ትተሃት የምትሄድ አጭር ቆይታ መሆኗን ባለ መርሳትና ያለህበት ድሎትም ሆነ መከራ ዘላለማዊ አለመሆኑን በማወቅ፣ለዘላለማዊቷ ጀነት ስንቅ የሚሆኑ ነገሮች ላይ አብዛኛውን ጊዜህን ለማሳለፍ ሞክር።

አላህ ሆይ ኻቲማችንን አደራ።

Copy from ሙከሚል አልወራቢይ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group