7 month Translate
Translation is not possible.

በጉራጌ ዞን ጌቶ ወረዳ የአላህን ቃል ቁርኣንን የሐፈዙ ተማሪዎች በድምቀት ተመረቁ!

(ሀሩን ሚድያ፦ ጥቅምት 11/2016)

በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በጉራጌ ዞን ጌቶ ወረዳ በሚገኘው እስኩት ዑመር መስጂድ ለሦስት ዓመታት የቁርኣን ሂፍዝ እና የተለያዩ ኪታቦችን የቀሩናየክረምት ኮርስ የወሰዱ ተማሪዎች ዛሬ ጥቅምት 11/2016 በታላቅ ድምቀት ተመርቀዋል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ሼህ አብዱሰላም አንዋር እንደተናገሩት የአላህን ቃል ቁርአንን ላፈዙ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትን እንዲሁም ያወቁትን እውቀት ለሌሎች እንዲያስተምሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ወንድም አብዱልሰላም ሀሠን በበኩሉ የእስኩት ዑመር መስጂድ በ1950 ዓ.ል እንደተመሠረተ በመግለፅ ከዛም በኾላ መስጂዱን በአዲስ መልክ በመገንባት በ2014 የእስኩት ዑመር ሂ ፍዝ ማዕከልን በማቋቋም 42 አዳሪ ተማሪዎች እና200 ተመላላሽ ተማሪዎች እያስተማረ እንደሚገኝ ገልፀዎል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ መጅሊስ ስራ አስፈፃሚ ሼህ አብዱል ሰላም አንዋር፣ሼህ ባህሩ ኡመርን ጨምሮ በርካታ ኡስታዞች፣ ዱዓቶች፣ተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል በዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይ ቁርኣንን ላፈዙ ተማሪዎች የሽልማት ስነስርዓት ተካሄድዋል።

¤ሀሩን ሚድያም በጉራጌ ዞን ጌቶ ወረዳ በእስኩት ዑመር መርከዝ የተገኘ ሲሆን ሙሉ ዝግጅቱን ወደእናንተ ምናደርስ ይሆናል።

...

©ሀሩን ሚዲያ

#islam #islamedia

image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group