Translation is not possible.

ከፈጣሪ ውጭ ለሌላ አካላት መሥዋዕት ማቅረብ።

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው!

® በኢሥላም ከአንዱ አምላክ ውጭ ለሌላ አካል መሥዋዕትን ማቅረብ በጥብቅ የተከለከለና የተረገመ ተግባር ነው።

“فصل لربك وانحر

ስለዚህ ለጌታህ ስገድ፤ (በስሙ) ሰዋም፡፡

[ 📚ሱረቱ አል-ከውሠር - 2 ]

قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

«ስግደቴ፣ መሥዋዕቴ ፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡

[📚6:162 ]

ከአሊይ ኢብኑ አቡ ጧሊብ {ረ•ዐ} እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብሏል

لَعَنَ اللَّهُ مَنْ ذَبَحَ لِغَيْرِ اللَّهِ

ከአሏህ ውጭ ለሌላ አካል "የሠዋን" (ያረደን) አሏህ ረግሞታል።

[📚ሰሂህ ሙሥሊም 1978]

® በክርስትናም ስንመለከት ከአንዱ አምላክ በስተቀር ለሌላ አካል መሥዋዕት ማቅረብ በጥብቅ የተከለከለ ብቻ ሳይሆን ይገደል የሚል ወፍራም ትዕዛዝ አለ።

“ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በቀር ለሌላ አማልክት የሚሠዋ ይጥፋ።”

  [📚ዘጸአት 22፥20 (አዲሱ መ.ት)

ይጥፋ ማለት ይገደል ማለት ነው።

‘እንዲጠፋ የተወሰነ ማንኛውም ሰው አይዋጅም፤ መገደል አለበት።”

[📚ዘሌዋውያን 27፥29 (አዲሱ መ.ት)

¶:- ይህ ሆኖ ሳለ ግን በክርስትና በተለይ በኦርቶዶክስ ለማርያም የአምልኮ መሥዋዕት ይቀርብላታል።

[📚እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 12 ቁጥር 98]

እመቤቴ ማርያም ሆይ ለአንቺ

የምስጋና እጅ መንሻን አቀርባለሁ

በመፍራችም እገዛልሻለሁ

በመስገድም እጅ እነሳልሻለሁ

የአምልኮ መሥዋዕንም ለአንቺ እሠዋለሁ።

[📚እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 13 ቁጥር 113]

እመቤቴ ማርያም ሆይ ያማረ ፍጹም ምስጋና አቀርብልሻለሁ

የሚጣፍጥ የአምልኮ መሥዋዕትንም አቀርብልሻለሁ።

፨፦ከፈጣሪ ውጭ ለማንም መሥዋዕት ማቅረብ ክልክል ሆኖ ሳለ ለማርያም የአምልኮ መሥዋዕት አቀርባለሁ እያላችሁ ማርያምን አናመልካትም ብላችሁ ስትከራከሩ አለማፈራችሁ ይገርማል።

وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ ۖ قَالَ سُبْحَانَكَ مَا يَكُونُ لِي أَنْ أَقُولَ مَا لَيْسَ لِي بِحَقٍّ ۚ إِن كُنتُ قُلْتُهُ فَقَدْ عَلِمْتَهُ ۚ تَعْلَمُ مَا فِي نَفْسِي وَلَا أَعْلَمُ مَا فِي نَفْسِكَ ۚ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّامُ الْغُيُوبِ

አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብላሃልን» በሚለው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ጥራት ይገባህ፤ ለእኔ ተገቢዬ ያልኾነን ነገር ማለት ለኔ አይገባኝም፡፡ ብዬው እንደ ኾነም በእርግጥ ዐውቀኸዋል፡፡ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፡፡ ግን አንተ ዘንድ ያለውን አላውቅም፡፡ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና» ይላል፡፡

(📚ሱረቱ አል-ማኢዳህ - 116)

✍ ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።

https://t.me/kNDk0

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group