Translation is not possible.

ዱንያ ላሰለቸቻችሁ.... ፈተና ተደራርቦ ተስፋ ላስቆረጣችሁ

ሁላችንም ህመሞች አሉን.... ዱንያ ለማንም ልትደላ አልተፈጠረችም..... ሁሌም ጎርባጣ ናት..... መፅናናት ከፈለግን ግን መፅናኛ አለ.... "አላህ ባሪያውን ሲወድ ይፈትነዋል" ከሁሉም በላይ የሆነ መፅናኛ ይመስለኛል። .... ከነ ጭንቀቱ በአላህ መወደድ ደስ አይልም? አያፅናናም?..... ከዛ ደሞ ዱንያ አላፊ መሆኗ ከፊታችን ጀነት መኖሩ አያፅናናም?..... አላህ ወደሱ አንድ ስንዝር ስንቀርብ እርሱ በእጥፍ መቅረቡ አያፅናናም?..... ስንለምነው የሚሠማን ጌታ መኖሩ አያፅናናም?.... የጠየቅነውን ባይሠጠን እንኳን ለአኼራችን አስቀምጦት መሆኑ አያፅናናም?.... ዱንያ ጎርብጣን ጎርብጣን የሆነ ቀን ስታበቃ በመታገሳችን ዘላለማዊዋ ጀነታችን መዋቧ አያፅናናም?

አዎ ዐቢድ ባሪያ ላንሆን እንችላለን.... የዱንያው መጎርበጥ ሳያንስ ታዛዥ ባሪያ መሆን እየተሳነን መኖራችን ወንጀል መጨመር መስሎ ሊሠማን ይችላል።.... ግን ጌታችን አላህ ነው። ያ ወዳድ የሆነው ወዱድ ❤️ ያ መጠጊያ የሆነው አስሠመድ ❤️ ያ ተውበትን ተቀባይ የሆነው አት ተዋብ❤️ ያ ይቅር ባይ የሆነው አል ዐፉው ❤️ ያ ወንጀል ባንሰራ እኛን አጥፍቶ ወንጀል ሠርተው ምህረት የሚጠይቁትን ይተካ እንደነበር የነገረን ❤️ ያ ከወንጀላችን ተመልሰን ተውበት ስናደርግ ግመሉ ስንቁን ይዛ በበረሀ ጠፍታበት ከተስፋ መቁረጥ በኋላ ስትገኝ ደስታ ጌታውን ባሪያ ካስደረገው ሠው በላይ የሚደሰት ነው ❤️.... እንዲህ አይነት ጌታ ያለው እንዴት ተስፋ ይቆርጣል?.... እንዲህ አይነት ጌታ ያለው እሱን መገናኘትን ይናፍቃል ፤ እሱን ማየት መጋረድን ይሰጋል እንጂ እንዴት ራሱን ማጥፋት ለዱንያ ችግር መፍትሄ እንደሆነ ይሠማዋል?...

ኢንሻአላህ ከፊታችን ቀናት አሉ... ያለቀስንባቸው ቀናት በደስታ የሚተኩበት.... ሀዘናችንን ልንነግረው የተደፋንለትን ጌታ ልናመሰግነው የምንሰግድለት.... ፀጋን ሁሉ የሚያስረሳውን የሱን ፊት ማየትን የምንታደልበት.... በባለአጎበር አልጋዎች ላይ ከወዳጆቻችን ጋር ሆነን ደስታችንን የምናጣጥምበት.... የምንወዳቸውን ነብይ ተጎራብተን ከሀውዳቸውም የምንጠጣበት.... ብዙ ብዙ ፀጋን .... ብዙዙ ብዙዙ ደስታን የምናጣጥምባቸው ቀናት ኢንሻአላህ ። 😍 አላህ ይወፍቀን 🤲

እስከዛው ልባችንን ይጠግንልን ፈተናውን ያቅልልን የምንቋቋምበትም አቅምን ይስጠን። 🤲

Sitina Amino Hulala

Send as a message
Share on my page
Share in the group